ሱዳን የአባይን ግድብ ለማጥቃት የሚነሳ ኃይል ካለ ከኢትዮጵያ ጋር እንደምትቆም ገለጸች

ሱዳን የአባይን ግድብ ለማጥቃት የሚነሳ ኃይል ካለ ከኢትዮጵያ ጋር እንደምትቆም ገለጸች

ኢትዮጵያ ነገ ዜና የአባይን ግድብ ለማጥቃት የሚነሳ ማንኛውም ኃይል ካለ ለመመከት አብረን እንቆማለን ሲሉ በሱዳን የ4ኛ ክፍለ ጦር ዋና አዛዥ ብርጋዴር ጀነራል ሁስማን ጁማ ተናገሩ።

ኢትዮጵያውያን እየገነቡት ያለውን የአባይን ግድብ ለማጥቃት የሚነሳውን ማንኛውም ኃይል  ለመመከት የሱዳን መንግሥትና ሕዝብ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጎን እንቆማለን ሲሉም የጦር አዛዡ አስረድተዋል።
በኢትዮጵያ የ22ኛ ንስር ክፍለ ጦር እና ከሱዳን የ4ኛ ክፍለ ጦር የጋራ ጥምር ወታደራዊ ኮሚቴ ለ13ኛ ጊዜ የሁለትዮሽ ውይይት ባካሄዱበት ወቅት ነበር ጀነራሉ ይህንን ንግግር ያደረጉት።
በድንበር አካባቢ ከሱዳን 4ኛ ክፍለ ጦር አመራሮች ጋር የመረጃ ልውውጦችን በማድረግ በተሰራው ስራ ድንበር ተሸጋሪ ወንጀሎችን በመከላከል ውጤታማ ሥራዎች መከናወናቸውን የ22ኛ ንስር ክፍለ ጦር ዋና አዛዥ ብርጋዲየር ጀነራል ነገሪ ቶሊና ተናግረዋል።
የጋራ ጥምር ወታደራዊ ኮሚቴው ፣ ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን በዘላቂነት ለመፍታት የሚያስችል የስምምነት ፊርማ የተፈራረመ ሲሆን ፣ ዓለም ዐቀፍ ወረርሽኝ የሆነውን ኮሮና ቫይረስን በጋራ በመከላከል የሁለቱ ሃገራት ሕዝቦች እንዲገናኙ ለማድረግም ይሠራልም ተብሏል።

LEAVE A REPLY