በፀጥታ ሀይሎች የሚወሰዱ የሀይል እርምጃዎች ከፍተኛ ጥንቃቄን ይሻሉ! || ኢሰመጉ

በፀጥታ ሀይሎች የሚወሰዱ የሀይል እርምጃዎች ከፍተኛ ጥንቃቄን ይሻሉ! || ኢሰመጉ

አስቸኳይ ጋዜጣዊ መግለጫ

በፀጥታ ሀይሎች የሚወሰዱ የሀይል እርምጃዎች ከፍተኛ ጥንቃቄን ይሻሉ!

ነሀሴ 20 ቀን 2012 ዓ.ም
ዜጎች ተቃውሟቸውን በሰላማዊ መንገድ የማቅረብ ሕገ-መንግሥታዊ መብት ያላቸው ሲሆን፣ መንግሥት
ደግሞ ይህን የማስከበር እና የማክበር ግዴታ ተጥሎበታል፡፡ በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ባለፈው ሰኔ መጨረሻ አካባቢ በተለያዩ አካባቢዎች ተፈጽመው በነበሩ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ተጎጂ የነበሩ ዜጎች ወደቀደመ ሁኔታቸው ሳይመለሱ እና ሳይቋቋሙ፣ ከሰሞኑ በክልሉ በተፈጠረ የጸጥታ ችግር የተነሳ የበርካታ ሰዎች ሕይወት የጠፋ መሆኑን ከስፍራው የሚወጡ እና ለኢሰመጉ የደረሱ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

ከነሀሴ 11 ቀን 2012 ዓ.ም አመሻሽ ጀምሮ በአሳሳ፣ በአዳባ፣ በዶዶላ፣ በሻሸመኔ፣ በባሌ ሮቤ፣ በጊኒር፣ በአሰቦት፣ በጭሮ፣ በአወዳይ እና በሌሎችም የክልሉ ከተሞች በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በተወሰዱየኃይል እርምጃዎች የዜጎች ህይወት ተቀጥፏል:: ይህ ተመጣጣኝነቱ አጠያያቂ የሆነ የጸጥታ ኃይሎች እርምጃ የሰብዓዊ መብቶች አያያዝ ሁኔታን ወደ አሳሳቢ ደረጃ እንዳይወስደው መንግስት በቂ ጥንቃቄ ሊወስድ እንደሚገባ ኢሰመጉ ያሳስባል፡፡..

LEAVE A REPLY