የኮምፒውተር ተህዋስ የተገጠመላቸው የቻይና ስልኮች አፍሪካ ውስጥ በከፍተኛ ደረጃ መሸጣቸው ተነገረ

የኮምፒውተር ተህዋስ የተገጠመላቸው የቻይና ስልኮች አፍሪካ ውስጥ በከፍተኛ ደረጃ መሸጣቸው ተነገረ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና–  53 ሺኅ ይህ ተህዋስ (ማልዌር) የተገጠመላቸው ቴክኖ ማርክ ያላቸው ቻይና ስሪት ስልኮች ኢትዮጵያ፣ ካሜሩን፣ ግብፅ፣ ጋና እና ደቡብ አፍሪካ ውስጥ መሸጣቸውን አፕስትሪም የተሰኘው ተቋም ይፋ አድርጓል።

እነዚህን ስልኮች አምራች የሆነው ትራንዚሽን የተሰኘው ኩባንያ ተህዋሱ የተገጠመው ከእኔ እውቅና ውጪ በአከፋፋዮች ነው በማለት እየተከራከረ ቢሆንም፤ አፕስትሪም የተሰኘው የመሰል ተህዋሶች አጋላጭ ድርጅት ግን በዚህ ሀሳብ እንደማይስማማ ገልጿል።
“ይህ ማልዌር (የኮምፒውተር ተህዋስ) በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ገቢያቸው አናሳ የሆኑ ሰዎች በሚገዙት ስልክ ላይ መሰል ተህዋስ ያለ ተጠቃሚዎች እውቅናና ፈቃድ ውጪ መገጠሙ ኢንዱስትሪው ምን ያክል የሰዎችን ግላዊነት እየተጋፋ እንዳለ የሚያሳይ ነው” በማለት የአፕስትሪም ባለሙያ የሆኑት ጄፍሪ ክሊቭስ ሀቁን ለማሳየት ምክረዋል።
ትሪያዳ የተሰኘው ተህዋስ አንድሮይድ ተንቀሳቃሽ ስልኮች ላይ የሚገጠም ሲሆን “ኤክስሄልፐር” የተባለ ኮድ ተጠቅሞ ከተጠቃሚዎች እውቅና ውጪ ያሻውን የሚያደርግ እንደሆነም ተነግሮለታል።
ማልዌሩ ብዙ ጊዜ ተጠቃሚዎች ሳያውቁ አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶችን የሚቀላቀል ከመሆኑ ባሻገር፤  ተህዋሱ ሞባይል ስልክዎ ላይ ያለዎትን ገንዘብ ወይም የአየር ሰዐት ያለ ፈቃድ የሚወስድ መሆኑ ታውቋል።

LEAVE A REPLY