የኮሮና ውጤት ባለመድረሱ በነጃዋር ላይ ሊሰማ የነበረው ምስክርነት ለአርብ ተቀጠረ

የኮሮና ውጤት ባለመድረሱ በነጃዋር ላይ ሊሰማ የነበረው ምስክርነት ለአርብ ተቀጠረ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ዛሬ ይጠበቅ የነበረው የአቶ ጃዋር መሀመድን ጨምሮ ስምንት ተጠርጣሪዎች ላይ ምስክር የመስማት ሂደት ወደ ሌላ ቀጠሮ ተቀየረ።

ከላይ የተጠቀሱትን ተከሳሾች ጨምሮ ሌሎች ተጠርጣሪዎች ላይ ቀሪ የዐቃቤ ህግ የቅድመ ምርመራ ምስክር ለመስማት ችሎቱ ለዛሬ የተቀጠረ ቢሆንም፤ ከ4ኛ እስከ 9ኛ ያሉ ተጠርጣሪዎች የኮሮና ቫይረስ የላቦራቶሪ ውጤት ከኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዪት ባለመምጣቱ ምስክሮችን ለማድመጥ ለነሃሴ 22 ቀን ተለዋጭ ቀጠሮ መሰጠቱ ታውቋል።
ዛሬ ችሎት ላይ የተገኘው ጃዋር መሀመድ ውጭ ሀገር ከሚገኙት ልጃቸው እና ባለቤታቸው ጋር በቪዲዮ ኮንፈረንስ አንድ ጊዜ ብቻ መገናኘቱን በመግለፅ በድጋሚ እንዲገናኙ እንዲፈቀድለት ጠይቋል።
ፍርድ ቤቱም በዚህ እና በተነሱ ሌሎች አቤቱታዎች ላይ በቀጣይ ቀጠሮ ትዕዛዝ እሰጥበታለሁ ሲል መደበኛ ሥራውን አጠናቋል።

LEAVE A REPLY