ማክስ 737 አውሮፕላኖችን ለመሞከር የአውሮፓ ኅብረት አቪየሽን ኤጀንሲ የጊዜ ሰሌዳ አወጣ

ማክስ 737 አውሮፕላኖችን ለመሞከር የአውሮፓ ኅብረት አቪየሽን ኤጀንሲ የጊዜ ሰሌዳ አወጣ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በእክል ምክንያት ከሥራ ውጭ ሆነው የቆዮት የቦይንግ ማክስ 737 አውሮፕላኖች በድጋሚ የሚሞከሩበት የጊዜ ሰሌዳን የአውሮፓ ኅብረት አቪየሽን ኤጀንሲ ማውጣቱ ተነገረ።

የአውሮፓ ኅብረት የአቪየሽን ደኅንነት ኤጀንሲ የማክስ 737 አውሮፕላኖች ሙከራዎች የሚካሄዱት ከመስከረም 7 ጀምሮ በካናዳ ቫንኩቨር መሆኑን ገልጿል።
በቦይንግ የአውሮፕላን ሽያጭ ታሪክ ተመራጭና ብዙ ገበያ እንደነበራቸው የሚነገርላቸው የቦይንግ ማክስ 737 አውሮፕላኖች ቴክኒካዊ እክል አለባቸው ተብለው ከገበያ እንዲወጡ የተደረጉት ባለፈው ዓመት በተለያዩ ሃገራት ተከስክሰው ለ346 ሰዎች ሞት ምክንያት ከሆኑ እንደሆነ አይዘነጋም።
የአውሮፓ አቪየሽን አውሮፕላኖቹን ለመሞከር የወሰነው የአሜሪካ አቪየሽን ተመሳሳይ ውሳኔ ላይ መድረሱን በመድረሱ እንደሆነ የሚወጡ መረጃዎች ያሳያሉ።
የሙከራ በረራው ቀደም ብሎ ሊካሄድ ይችል እንደነበረ የገለጸው አቪየሽኑ ፤ የኮቪድ-19 መከሰት፣ በአውሮፓና አሜሪካ የበረራ ግንኙነት መስተጓጎል የሙከራ ጊዜውን ለመግፋት አስገድዶት እስካሁን እንዳቆየው አስታውቋል።
 በቫንኩቨር እንዲሁም ከመስከረም አንድ ጀምሮ ደግሞ በለንደን ጋትዊክ አየር መንገድም ተመሳሳይ የበረራ ሙከራ ለማድረግ እቅድ እንደተያዘ በመነገር ላይ ነው።
በተያያዘ መረጃ የአሜሪካ የፌዴራል አቪየሽን አስተዳደር ማክስ 737 አውሮፕላንን ዳግም ወደ አየር ለመመለስ በርካታ ቅድመ ሁኔታዎችን ማስቀመጡ እየተነገረ ነው።
የበረራ ቁጥጥር ሶፍትዌርን ማሻሻልና ሌሎች ዘርዘር ያሉ ውስብስብ ቴክኒካዊ ጉዳዮች በቅድመ ሁኔታ የተቀመጡ ናቸው።
ቦይንግ በሚቀጥለው የፈረንጆት ዓመት መጀመሪያ በነበረባቸው እክል ተሳፋሪዎቻቸውን ለሞት የዳረጉት የ737 ማክስ አውሮፕላኖች ወደ በረራ እንደሚመለሱ እቅድ ይዞ እየሠራ ነው።

LEAVE A REPLY