ዛሬ ተጨማሪ 1ሺኅ 186 ሰዎች የኮሮናቫይረስ ሲገኝባቸው፤ 20 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል

ዛሬ ተጨማሪ 1ሺኅ 186 ሰዎች የኮሮናቫይረስ ሲገኝባቸው፤ 20 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ባለፉት 24 ሰዐታት ውስጥ ለ18 ሺኅ 060 ሰዎች በተደረገ የላቦራቶሪ ምርመራ 1 ሺኅ 186 ሰዎች የኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር ገለጸ።

ይህን ተከትሎ በአጠቃላይ በሃገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 46 ሺኅ 407 ደርሷል።
በአንጻሩ በትናንትናው ዕለት ሰዎች ያገገሙ 518 ሲሆን፣ በአጠቃላይ በአገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 16 ሺኅ 831 መድረሱ ታውቋል።
በተያያዘ ዜና ባለፉት 24 ሰዐታት ምርመራ የ20 ሰዎች ሕይወት ማለፉን ተከትሎ በኮሮና ቫይረስ የተነሳ የሟቾች ቁጥር 745 መድረሱን የኢፌዲሪ ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።
በአሁኑ ወቅት 330 ሰዎች በጽኑ ሕክምና ላይ ሲገኙ፣ 28 ሺኅ 831 ደግሞ ቫይረሱ ያለባቸው ሰዎች መሆናቸው ተረጋግጧል።

LEAVE A REPLY