የአ/አ ከተማ አስተዳደር የሰላም ምክር ቤት ዛሬ በይፋ መሠረተ

የአ/አ ከተማ አስተዳደር የሰላም ምክር ቤት ዛሬ በይፋ መሠረተ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– አዲስ ከንቲባ የተሾመለት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሰላም ምክር ቤት ዛሬ በይፋ መመስረቱን አስታወቀ።

የከተማዋ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ እና የሁሉም ክፍለ ከተሞች የተውጣጡ ባለድርሻዎች በምስረታ ፕሮግራሙ ላይ መገኘታቸውን የከተማዋ ፕሬስ ሴክሪተሪያት ቢሮ አስታውቋል።
የሰላም ምክር ቤቱ መመስረት ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል የሚል እምነት እንደተጣለበት ከወዲሁ ተነግሮለታል።
በሰላም ምክር ቤት ማቋቋሚያ መመስረቻ መርሃ-ግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ፤ የበርካታ ዓለም ዐቀፍ ተቋማት መቀመጫ የሆነችው መዲናችን አዲስ አበባ የነዋሪዎቿን ሰላም በአስተማማኝ ሁኔታ ማረጋገጥ የምክር ቤቱ መሠረታዊ ተግባር እንደሆነ ገልጸዋል።
በአዲስ አበባ የሰላም ጠንቅ የሆኑ የምሽት ቅሚያን ጨምሮ የተሽከርካሪ ስርቆት፣ በቡድን በመደራጀት የኅብረተሰቡን ሰላም የማደፍረስ እና ህገ-ወጥ የመሬት ወረራ ላይ የማያዳግም እርምጃ በመውሰድ የነዋሪውን ሰላም ማረጋገጥ ይገባል ሲሉም አዲሷ ከንቲባ ተናግረዋል።
ምክር ቤቱ በወረዳ ደረጃ 300፣ በክፍለ ከተማ 400 እና በከተማ ደረጃ 500 አባላትን አቅፎ ፤ በከተማዋ እየተፈጸሙ ያሉ የወንጀል ድርጊቶችን በቅንጅት ለመፍታት ይሠራል ተብሏል።

LEAVE A REPLY