የሃጫሉ ሁንዴሳ ገዳዮች ላይ ክስ እንዲመሠረት 15 ቀን ጊዜ ተፈቀደ

የሃጫሉ ሁንዴሳ ገዳዮች ላይ ክስ እንዲመሠረት 15 ቀን ጊዜ ተፈቀደ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳን በመግደል በተጠረጠሩት ከበደ ገመቹና አብዲ ዓለማየሁ ላይ ዐቃቤ ህግ ክስ እንዲመሰርት የ15 ቀን ጊዜ መሰጠቱ ታወቀ።

በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ተረኛ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ፖሊስ ምርመራውን በማጠናቀቅ  መዝገቡን ለዐቃቤ ህግ ያስረከቡ ሲሆን፤ በችሎቱ አንደኛው ተጠርጣሪ አብዲ ዓለማየሁ አርቲስት “ሃጫሉ በተገደለበት ወቅት በቦታው አልነበርኩም” ሲል ቢከራከርም፤ ሌላኛው ተጠርጣሪ ጥላሁን ያሚ በበኩሉ አርቲስቱ ሲገደል ከበደ ገመቹ እና አብዲ ዓለማየሁ አብረውት እንደነበሩ የእማኝነት ቃሉን ሰጥቷል።
ይህን ተከትሎ ፍርድ ቤቱ በተጠርጣሪዎቹ ላይ ክስ መመስረቻ የ15 ቀን ጊዜ መስጠቱን ዛሬ የወጡ መረጃዎች ያሳያሉ።

LEAVE A REPLY