የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ የገዳ ሥርዓትን በመደበኛ ትምህርት ዓይነት ለመስጠት ተዘጋጅቻለሁ አለ

የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ የገዳ ሥርዓትን በመደበኛ ትምህርት ዓይነት ለመስጠት ተዘጋጅቻለሁ አለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና በአዲስ አበባ “የገዳ ሥርዓት” ትምህርትን በመደበኛነት ለመስጠት መመሪያ መውጣቱ ተሰማ።

በለውጡ ማግስት የአዲስ አበባ ከተማን የተለያዮ ወሳኝ ቦታዎች የተቀራመቱት የኦዴፓ አባላት በከተማዋ ላይ የተረኝነት ስሜትን በሕዝብ ዘንድ የሚያሰርጹ ሥራዎችን በቅርቡ ከሓላፊነታቸው ከተነሱት ከንቲባው ጀምሮ ሲተገበር መቆየቱ ተዘግቧል።
አሁን ላይ የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ የገዳ ሥርዓትን እንደ አንድ የትምህርት አይነት በመዲናዋ ሁሉም ትምህርት ቤቶች ለመስጠት እየተዘጋጀሁ ነው ማለቱ ተሰምቷል።
የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ወደ ፊት የገዳ ትምህርትን ለሁሉም ተማሪዎች ሊሰጥ እንደሚችል ጠቁሞ፤ ይህ የሚሆነው ግን በቅድሚያ በከተማዋ ላሉ የኦሮምኛ ተማሪዎች በማስተማር እና ውጤታማነቱ ከተፈተሸ በኋላ እንደሆነም ይፋ አድርጓል።
ትምርህቱን ለሁሉም ተማሪዎች ከመሰጠቱ በፊት ግን ሕብረተሰቡ እንዲወያይበት ይደረጋል የሚለው የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ፤ ትምህርቱ መቼ  እድሚሰጥ ግን በትክክል የገለጸው ነገር የለም።

LEAVE A REPLY