ለግል ኩባንያዎች በዱቤ ነዳጅ የመስጠት አሠራር በኢትዮጵያ ሊቆም ነው ተባለ

ለግል ኩባንያዎች በዱቤ ነዳጅ የመስጠት አሠራር በኢትዮጵያ ሊቆም ነው ተባለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ለግል ኩባንያዎች በዱቤ የሚያቀርበውን የነዳጅ አቅርቦት ለማስቀረት እየሠራሁ ነው አለ።

ከእንግዲህ በኋላ የነዳጅ አከፋፋይ ኩባንያዎች የሚፈልጉትን ያህል ነዳጅ ክፍያውን ፈጽመው መውሰድ እንዲገደዱ ሊደረግ መሆኑን፣ ጥያቄም ለመንግሥት ቀርቦ መልስ እየተጠበቀ እንደሚገኝ ተነግሯል።
ጠቅላላ የነዳጅ አቅርቦቱ የዱቤ ሥርዓት እንዲቀር ታሳቢ ተደርጎ እየተሠራ በመሆኑ፤ ከዚህ ቀደም እዳ ያለባቸው የግል ኩባንያዎችም እንዴት ወደ መስመሩ  እንደሚገቡም በጥልቀት እየታሰበበት ነው ተብሏል።
በኢትዮጵያ የነዳጅ አቅርቦትና የዱቤ ሽያጩ ከሰባ ዓመት በላይ የነበረ እንደመሆኑ መጠን በዛው ልክ ችግሩም ቢሆን እየተሠራበት እንደነበር ነዳጅ አቅራቢ ድርጅቱ አስታውቋል።
ይህንን ተከትሎ ሁሉም ኩባንያዎች ወደ ቀጥተኛ ንግድ እንዲገቡ በማድረጉ ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ ሲሆን፤ ከዚህ ቀደም ከፍተኛ የሆነ እዳ የነበረባቸው አምስት የግል ኩባንያዎችም አሁን እዳቸውን እየከፈሉ እንደሚገኙ ተቋሙ አረጋግጧል።

LEAVE A REPLY