የህዳሴው ግድብ ድርድር ተስፋ ሰጪ ውጤት ታየበት ተባለ

የህዳሴው ግድብ ድርድር ተስፋ ሰጪ ውጤት ታየበት ተባለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና ኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብጽ በህዳሴው ግድብ ግንባታ ዙሪያ ባለፉት ሁለት ሳምንታት ሲካሄድ በነበረው ድርድር ላይ የተወሰነ ውጤት ታይቷል ተባለ።

የኢትዮጵያ ውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ፤ ምንም እንኳን በድርድሩ ውጤቶች እየታዩ ቢሆንም የሚጠበቀውን ረቂቅ የስምምነት ሰነድ ለማቅረብ ፍጻሜ ላይ አልተደረሰም ሲሉ ገልጸዋል።
ጉዳዮን አስመልክቶ የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ፤ የሦስቱ ሃገራት የውሃ ጉዳይ ሚኒስትሮች ትናንት አርብ ውይይት መካሄዱንና ባለፉት ቀናት በባለሙያዎች መካከል ሲካሄድ የነበረው ድርድር ውጤት ሪፖርት መቅረቡን አስታውቋል።
የኢትዮጵያ፣ የሱዳንና የግብጽ ባለሙያዎች ከነሐሴ 15/2012 ዓ.ም ጀምሮ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ አሞላልና የውሃ አለቃቀቅ ደንብ ላይ ድርድር ሲያካሂዱ መቆየታቸውን ተከትሎ የውይይቱ ውጤት ለሃገራቱ ሚኒስትሮች ቀርቧል ያለው መግለጫ፤ በሚኒስትሮቹ ስብሰባ ላይ የደቡብ አፍሪካ፣ የአውሮፓ ኅብረትና የአሜሪካ ተወካዮች ታዛቢ ሆነው ከመገኘታቸው ባሻገር፣ የአፍሪካ ኅብረት የወከላቸው ባለሙያዎችም እንደነበሩ ይፋ አድርጓል።
ኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብፅ እየተካሄደ ያለውን ድርድር ቀጣይ ሂደት በተመለከተም ለደቡብ አፍሪካ ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር እንዲሁም ለአፍሪካ ኅብረት የአስፈጻሚ ምክር ቤት ሊቀ መንበር በደብዳቤ ለማሳወቅ ከስምምነት ላይ መድረሳቸው ተሰምቷል።
ይህ የሦስቱ አገራት ድርድር ሂደት ከሱዳን በኩል የሚሰጥ ማረጋገጫን መሰረት በማድረግ መስከረም 04/2012 ዓ.ም እንደሚቀጥል ነው የተነገረው።

LEAVE A REPLY