ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አዲሱን የፌዴራል ፖሊስ የደንብ ልብስ ዛሬ በይፋ አስተዋወቀ።
የፀጥታ ተቋሙ የደንብ ልብሱን በአዲስ መቀየር ያስፈለገበት ምክንያት ልብሱ ለረጅም ዓመታት አገልግሎት ላይ በመቆየቱ መሆኑን የደንብ ልብሱን ይፋ ያደረጉት የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄኔራል እንደሻው ተናግረዋል።
በተያያዥነት በቀድሞው የደንብ ልብስ ተጠቅመው የተለያዩ ወንጀሎች የሚፈፀሙ አካላት በዚህ ወቅት መጨመራቸው ለዮኒፎርሙ መቀየር በምክንያትነት ቀርቧል።
ከዚህ በተጨማሪ የፌዴራል ፖሊስ አባላት በአዲሱ 2013 ዓ.ም በአዲስ መንፈስና ወደ ሥራ እንዲገቡ የታሰበ መሆኑንም ሓላፊው ገልጸዋል።
በደንብ ልብሱ ይፋዊ የምረቃ ሥነ ሥርዓት ላይ በእንግድነት የተገኙት የሰላም ሚኒስትሯ ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል፤ የፖሊስ የደንብ ልብስን መቀየር እንደ ሀገር የተጀመረው ሪፎርም አካል ነው ሲሉ ተነግረዋል።