ሞፈሪያት ካሚል ባለመፈረማቸው ኢዜማ በራስ ሆቴል ሊሰጥ የነበረው ጋዜጣዊ መግለጫ ተከለከለ

ሞፈሪያት ካሚል ባለመፈረማቸው ኢዜማ በራስ ሆቴል ሊሰጥ የነበረው ጋዜጣዊ መግለጫ ተከለከለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) በአዲስ አበባ እየተደረገ ነው ያለውን የመሬት ወረራና ህገ-ወጥ የጋራ መኖሪያ ቤቶች እደላ በተመለከተ ሊሰጠው የነበረው ጋዜጣዊ መግለጫ ዛሬም ዳግመኛ በመንግሥት ተከለከለ።

የኢዜማ የሕዝብ ግንኙ ሓላፊ አቶ ናትናኤል ፈለቀ መግለጫው የተከለከለው፤ መግለጫ የሚሰጥበት ቦታ የሆነው ራስ ሆቴል “ከሰላም ሚኒስቴር የተፃፈ ደብዳቤ ስጡኝ” በማለቱ፤ የሰላም ሚኒስትር ደግሞ ደብዳቤ ለመፃፍ ባለመፍቀዱ እንደሆነ ተናግረዋል።
ባለፈው አርብ ፓርቲው ጋዜጣዊ መግለጫ ለመስጠት አስፈላጊውን መሰናዶ በፈጸመበት ወቅት ራስ ሆቴል እንዲህ ዓይነት ጥያቄ አለማቅረቡ የሚታወስ ነው።
ኢዜማ ለሁለተኛ ጊዜ መግለጫ እንዳይሰጥ ቢከለከልም መግለጫውን በፅ/ቤቱ ዛሬ ከሰዐት በኋላ በፓርቲው ጽ/ቤት መስጠት ችሏል።
የኢዜማን የጋዜጣዊ መግለጫ ደብዳቤ የፈቃድ ደብዳቤ አልጽፍም ያለው የሰላም ሚኒስቴር ፤ የሚኒስትሯ ጽህፈት ቤት ፈቃዱን የሚሰጠው አካል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የሚኒስትሮች ኮሚቴ መሆኑን ጠቁሞ ለኢዜማ ደብዳቤው ያልተፃፈለት ፣ ሚኒስትሯ (ሞፈሪያት ካሚል) ስለሌሉ ነው የሚል አስገራሚ ምላሽ ለሸገር ራዲዮ ሰጥቷል ፡፡
ጉዳዮን አስመልክቶ ማብራሪያ በደብዳቤው ላይ የሚፈርሙት ሚኒስትሯ ስለሌሉ ነው እንጂ፣ ኢዜማ ፈቃድ አልተከለከለም ሲል ይፋ አድርጓል።

LEAVE A REPLY