በመስከረም ወር የነዳጅ ችርቻሮ መሸጫ ባለበት እንዲቀጥል ተወሰነ

በመስከረም ወር የነዳጅ ችርቻሮ መሸጫ ባለበት እንዲቀጥል ተወሰነ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በመጪው መስከረም ወር በኢትዮጵያ  የነዳጅ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ባለበት እንዲቀጥል መወሰኑ ተሰማ።

የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ዛሬ ባወጣው መግለጫ በሚቀጥለው መስከረም ወር ከአውሮፕላን ነዳጅ ውጪ የሌሎች የነዳጅ ምርቶች ዋጋ ባለበት ይቀጥላሉ ብሏል።
የአውሮፕላን ነዳጅ ዋጋ በመስከረም ወር በሊትር 26.97 ብር እንዲሆን መወሰኑም ታውቋል።
በዓለም ገበያ ላይ የሚኖረውን የነዳጅ ዋጋ መነሻ በማድረግ የአውሮፕላን ነዳጅ ዋጋ እንደ አስፈላጊነቱ ማስተካከያ ሊደረግበት እንደሚችል የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር እወቁልኝ ሲል ገልጿል።

LEAVE A REPLY