አሜሪካ 130 ሚሊዮን ዶላር ያገደችው ከህዳሴው ግድብ ጋር በተያያዘ ነው ተባለ

አሜሪካ 130 ሚሊዮን ዶላር ያገደችው ከህዳሴው ግድብ ጋር በተያያዘ ነው ተባለ

 ኢትዮጵያ ነገ ዜና አሜሪካ ቀደም ሲል ለኢትዮጵያ ልትሰጥ አቅዳው የነበረው የገንዘብ ድጋፍ እንዳይሰጥ የተደረገው በጊዜያዊነት መሆኑን በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር የሆኑት አቶ ፍጹም አረጋ ገለጹ።
አምባሳደር ፍጹም አረጋ በማኅበራዊ ሚዲያ ገጾቻቸው ላይ ባሰፈሩት ጽሑፍ፤ የገንዘብ ድጋፉ የተያዘው ለአጭር ጊዜ መሆኑን ከሚመለከታቸው የአሜሪካ መንግሥት ኃላፊዎች ተነጋግረው መረዳታቸውን አስነብበዋል።
አሜሪካ ለኢትዮጵያ የመደበችው 130 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር እንዳይሰጥ መወሰኗ ከተሰማ በኋላ ስለጉዳዩ ማብራሪያ እንዲሰጣቸው መጠየቃቸውን የጠቆሙት አምባሳደር ፍጹም፤  በዚሁ መሰረት ገንዘቡ በጊዜያዊነት እንዳይሰጥ መደረጉጥንና የገንዘቡ እግድም ከሕዳሴው ግድብ ግንባታ ጋር በተያያዘ መሆኑን መገንዘባቸውን ገልጸዋል።
አስቀድሞ ይህንን የአሜሪካ መንግሥትን ውሳኔ በተመለከተ ይፋ ያደረገው ፎሬይን ፖሊሲ የተባለው መጽሔት ሲሆን፤ መጽሔቱ አሜሪካ ለኢትዮጵያ ለመስጠት የመደበችውን 130 ሚሊዮን ዶላር ላለመስጠ መወሰኗን የውስጥ ምንጮቼ  አረጋግጠውልኛል ሲል መዘገቡ አይዘነጋም።

LEAVE A REPLY