ኢዜማ የመሬት ወረራና ኮንዶሚኒየም ዕደላውን አስመልክቶ የወንጀል ይጣራልኝ አቤቱታ አቀረበ

ኢዜማ የመሬት ወረራና ኮንዶሚኒየም ዕደላውን አስመልክቶ የወንጀል ይጣራልኝ አቤቱታ አቀረበ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) የአዲስ አበባ የመሬት ወረራና የኮንዶሚኒየም እደላ ህገ-ወጥነትን ተከትዬ ባደረኩት ጥናት መሰረት የወንጀል ይጣራልኝ አቤቱታ አቅርቤያሁ ማለቱ ተሰማ።

የፓርቲው የድርጅት ጉዳይ ሓላፊ አቶ ዋሲሁን ተስፋዬ ግኝታችንን መሰረት አድርገን የወንጀል ይጣራልን አቤቱታ ለ3 ተቋማት አቅርበናል ሲሉ ጉዳዮ ወደ ሕግ አግባብ እንዲወሰድ እንቅስቃሴ መጀመሩን ይፋ አድርገዋል።
በፕ/ር ብርሃኑ ነጋ የሚመራው ኢዜማ የአዲስ አበባ ጉዳይ አሳስቦኛል፣ የመሬትና የኮንዶሚኒየም ህገ-ወጥ እደላው ነገርም አሳሳቢ ከሆኑ ነጥቦች መሀከል አንዱ ነው ሲል ከተደጋጋሚ ክልከላ በኋላ ትናንት በጽ/ቤቱ በሰጠው መግለጫ ላይ ይፋ ማድረጉ አይዘነጋም።
የታከለ ኡማ አስተዳደር ባለፉት ሁለት ወራት ከተረኝነት ፖለቲካ ጋር በተያያዘ ሲፈጽመው ቆይቷል ያለውን በደል ያጋለጠው ኢዜማ ፤ የወንጀል ይጣራልኝ አቤቱታ ያቀረብኩት ለጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ፣ ለፌዴራል ሥነ-ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽንና ለፌዴራል ፖሊስ ነው ብሏል።

LEAVE A REPLY