ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– በአዲስ አበባ ቦሌ ኤርፖርት በህገ ወጥ መንገድ በቀጥታ ሊገባ የነበረ ሠባት ስናይፐር ወደ ሃገር ሊገባ ሲል መያዙ ተሰማ።
ስናይፐሩ የተያዘው በተበታተነ መልኩ በቦርሳዎች ከሌሎች እቃዎች ጋር ተጠቅልሎ ለማለፍ በተደረገ ጥረት እንደሆነም ተገልጿል።
ነሐሴ 25/12/12 ዓ.ም በቦሌ ኤርፖርት ዓለም ዐቀፍ በረራ መግቢያ በኩል ከሳዑዲ አረቢያ የመጣ አንድ ግለሰብ ሲሆን፤ ግለሰቡ ከኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ ቆንጽላ ጽ/ቤት ጅዳ ጠቅልለዉ ወደ ሀገራቸዉ እንደሚገቡና የሚይዙት የግል መገልገያ ዕቃ ከቀረጥና ታክስ ነፃ እንዲሆንላቸዉ ደብዳቤ ይዘው እንደነበርም ይፋ ተደርጓል።
ግለሰቡ አጋጣሚውን በመጠቀም ከግል መገልገያ ዕቃዎቻቸዉ ጋር ተገጣጥሞ ለ7 የስናይፐር ጦር መሳሪያ የሚሆኑ ክፍሎችን በታትነው በተለያዩ ሻንጣዎች ዉስጥ ደብቀዉ ለማሳለፍ ሲሞክሩ፤ በቦሌ ኤርፖርት ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት አማካኝነት በቁጥጥር ሥር መዋሉ ተረጋግጧል።