ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– የአማራ ብድርና ቁጠባ ተቋም ለዘጠኝ ዓመት ሲጠይቀውና ሲከራከርበት የቆየው የሽግግር ጥያቄ ምላሽ አግኝቶ ተቋሙ ወደ ባንክ ማደጉ ታወቀ።
የተቋሙ ዋና ስራ አስፈፃሚ መኮንን የለውም ወሰን፤ ተቋሙ ወደ ባንክ ሲሸጋገር በ8 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር መነሻ ካፒታል ሥራ እንደሚጀምርና በ53 ነባር የተቋሙ ቅርንጫፎች ተደራሽ እንደሚሆንም ገልጸዋል።
ባንኩን ከ3 እስከ 6 ወር ባለ ጊዜ ውስጥ ሥራ ለማስጀመር ሥራ እየተሠራ መሆኑን ዋና ሥራ አስፈጻሚው ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ መረዳት ችለናል።
በብድር ተቋሙ ላይ የክልሉ መንግሥት ድርሻ 98 በመቶ የነበረ ሲሆን ፤አሁን ግን ወደባንክ ሲያድግ ከ70 በመቶ መብለጥ እንደሌለበት መመሪያው ሲለሚገድብ 30 በመቶው ለግል አክሲዮን የሚሸጥ መሆኑም ተሰምቷል።