ታከለ ኡማ 20 ሺኅ ኮንዶሚኒየሞችን ለአርሶ አደሮች ነው ያከፋፈልኩት ሲሉ አስተባበሉ

ታከለ ኡማ 20 ሺኅ ኮንዶሚኒየሞችን ለአርሶ አደሮች ነው ያከፋፈልኩት ሲሉ አስተባበሉ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና በሥልጣን ዘመናቸው የፈጸሙት የዘር ትስስር ተግባር ትናንት በኢዜማ ገሀድ የወጣባቸው የቀድሞው የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ ማስተባበያ ሰጡ።

የአሁኑ የማዕድን ሚኒስተቴር ሚኒስትር ኢ/ር ታከለ ኡማ  በቀጥታ የኢዜማን የግኝት ጥናት ባይጠቅሱም በጉዳዮ ላይ ራሳቸውን ነጻ ያደረገ ምላሽ ዛሬ በፌስ ቡክ ገጻቸው ላይ አስነብበዋል።
“የመሬት ወረራን በተመለከተ ከመጀመሪያዋ ቀን ጀምሮ እስከ መጨረሻዋ እለት ድረስ ጠንካራ የሆነ እርምጃ ስንወስድበት የቆየንበት ጉዳይ ነው” ያሉት ታከለ ኡማ፤ ለ20ሺኅ አርሶ አደሮች የተሰጡ የኮንዶሚኒየም ቤቶችን በተመለከተም ከአንድ አመት ተኩል በፊት በካቢኔ የተወሰነና የተተገበረ መሆኑን ተናግረዋል።
 ከመሬታቸው ላይ ተፈናቅለው በዝቅተኛ ሥራ ላይ ተሰማርተው የነበሩ 67 ሺኅ አባወራዎች ነበሩ ያሉት የቀድሞው ከንቲባ፤ “የከፋ ችግር ላይ ለወደቁት 20 ሺኅ ኮንዶሚንየም ሰጥተናል፤ ይህ ተግባር  ቢያንስ እንጂ የሚበዛ አይደለም” ሲሉ አስገራሚ ምላሽ ሰጥተዋል።
በዚህ ተግባራቸው እንደሚኮሩ የጠቆሙት ታከለ ኡማ “በግፍ የተገፋን፣ በግፍ ከመሬቱ የተፈናቀለን አርሶ አደር መካስ ያኮራናል!” ሲሉም አቋማቸው ትክክል እንደነበር ይታወቃል።
 ” አንድም ቀን በግፍ ለተፈናቀሉ አርሶጰአደሮች የመቆርቆር ስሜት አሳይቶ የማያውቅ ቡድን ዛሬ የአርሶ አደሮችን ጉዳት ለተቀባይነት ማግኛ መጠቀሚያ ሲያደርገው ማየት ” ያሳዝናል ሲሉም የቀድሞው ከንቲባ ኢዜማን ስም ባይጠቅሱም በነገር ሸንቆጥ አድርገዋል።

LEAVE A REPLY