ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– ባለፉት 24 ሰዐታት በተደረገ 18 ሺኅ 160 የላብራቶሪ ምርመራ 1ሺኅ 173 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን የጤና ሚኒስትር አስታወቀ።
በሌላ በኩል ባለፋት 24 ሰዐታት የ19 ሰዎች ሕይወት በቫይረሱ ማለፉን ተከትሎ አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 828 ደርሷል።
በአንጻሩ በትናንትናው ዕለት 493 ሰዎች ማገገማቸው የተነገረ ሲሆን፤ ይህም ከበሽታው ያገገሙ ሰዎችን ቁጥር 19 ሺኅ 487 እንዳደረሰው ተሰምቷል።
በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 53 ሺኅ 304 እንደደረሰ የጤና ሚኒስቴር በእለታዊ ሪፖርቱ ይፋ አድርጓል።