ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የዘር ማጥፋት መከላከያ ተቋም መቋቋሙ ታወቀ።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ተከታዮችን በሃይማኖታቸው፣ በዘራቸውና በማንነታቸው ለይቶ ለማጥፋት እየተፈጸመ ያለውን ወንጀል ለመከላከል ተመሳሳይ አቋም ካላቸው ዓለም ዐቀፍ ተቋማት ጋር በትብብር ለመሥራት ነው የመከላከያ ቡድኑ የተቋቋመው።
“SAGE “የተባለው ዓለም ዐቀፍ ድርጅትና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በአንድነት ለመሥራት ስምምነት እንደፈጸሙ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰሜን ካሊፎርንያ ነቫዳ አሪዞና አገረ ስብከት ገልጿል።
የተቋቋመው ድርጅት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የዘር-ጥፋትን መከላከያ ተቋም (ኢተከዘተ) በመባል የሚጠራ መሆኑን የጠቅመው ሀገረ ስብከቱ፤ በቡድኑ የሃይማኖት አባቶች፣ ምሁራን፣ ወጣቶች እና የሃገር ሽማግሎች የተካተቱበት መሆኑንም ይፋ አድርጓል።