የገርጂ የቤት ልማት ፕሮጀክት ሲጀምር ከቦታው የሚነሱ ነዋሪዎች የሉም ተባለ

የገርጂ የቤት ልማት ፕሮጀክት ሲጀምር ከቦታው የሚነሱ ነዋሪዎች የሉም ተባለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ባለፈው ሳምንት ይፋ የተደረገው የገርጂ የቤት ልማት ፕሮጀክት በጳጉሜ ወር (ቀጣዮ ሳምንት) እንደሚጀምር ተረጋገጠ።

ከ28 ዓመት በኋላ ዳግም ሥራ የጀመረው የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን በሚቀጥለው ሳምንት ግንባታው የሚጀምር መሆኑን ይፋዋ ማረገገጫ ሰጥቶበታል።
ቤቶቹ የሚገነቡት በቦሌ ክፍለ ከተማ ገርጂ ሮባ ዳቦ ቤት አካባቢ መሆኑ አስቀድሞ መገለጹን የጠቆመው ኮርፖሬሽኑ ለሥራውም ተብሎ የሚነሱ የኅብረተሰብ ክፍሎች እንደማይኖሩ አስታውቋል።
የመንግሥት ሠራተኞች  መኖሪያ እጥረትን ለመቅረፍ የሚገነባው ህንጻ የሚቆምበት ሥፍራ ቀደም ሲል ለተለያዮ ባለሀብቶች (የትግራይ ተወላጆችና የህወሓት አባላት) ለልማት ተመርቶ የነበረና በለውጡ ማግስት ወደ መሬት ባንክ እንዲገባ የተደረገ መሆኑን ታማኝ ምንጮቻችን ለኢትዮጵያ ነገ ገልጸዋል።
በሦስት ሄክታር ላይ 510 ቤቶችን በ3 ቢሊዮን ብር ለመገንባት ያሰበው የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን በግንባታው ላይ የተለያዮ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን እንደሚጠቀም ማስታወቁ አይዘነጋም።

LEAVE A REPLY