ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– ግሎባል ኢንሺራንስ ኩባንያ የሸሪዓ ህግጋትን የተከተለ “ታካፉል” የተባለ ከወለድ ነፃ የመድህን ሽፋን አገልግሎት መክፈቱ ተሰማ
አዲሱ አገልግሎት በሁሉም ቅርንጫፍ መሥሪያ ቤቶች የሚሰጥ ሲሆን፣ አዋጭነቱ በጥናት ተረጋግጦ ወደ ሥራ መገባቱም ይፋ ተደርጓል።
ግሎባል ኢንሹራንስ ኩባንያ በኢንሹራንስ ዘርፉ ለመጀመሪያ ጊዜ የሸሪዓ ህግና መርሆዎን መሰረት ያደረገ ትርፍን የሚያጋራ፣ እስላማዊ አስተምህሮን የተከተለ ከወለድ ነፃ የሆነ የመድህን ሽፋን አገልግሎት እንደጀመረ ነው የተገለጸው።
በፕሮግራሙ ላይ የተገኙ የባንኮች ከፍተኛ የሥራ ሓላፊዎች በባንኮች ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት እየተሰጠ ቢሆንም የሸሪዓ ህግጋትን የተከተለ የኢንሹራንስ አገልግሎት ባለመኖሩ ግን ቅሬታን ሲፈጥር መቆየቱን አስታውሰዋል።
ከዚህ በፊት በመደበኛ የባንክ እና የኢንሹራንስ አገልግሎት መገልገል የማይፈልጉ ሰዎች ገንዘባቸውን ቤታቸው ውስጥ ለማስቀመጥ ይገደዱ እንደነበር የገለጹት የኢትዮጵያ አካውንቲንግና ኦዲት ቦርድ ዳይሬክተር ወ/ሮ ሂክመት አብደላ፤ ተቋሙ ይህንን በመክፈቱ ቤት የሚቀመጡ ብሮች ወደ ፋይናንስ ሥርዓት ውስጥ በመግባት ለሀገሪቱ ዕድገት አስተዋጽዖው የጎላ ይሆናል ብለዋል።
በፋይናንስ ዘርፉ ላይ የተደረገው የማሻሻያ ሥራዎች የፋይናንስ ተቋማት ሁሉንም ያማከለ አገልግሎት እንዲሰጡ እድል ከፍቶላቸዋል መባሉንም ሰምተናል።