ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– በተደጋጋሚ በአስከፊ ሁኔታ ውስጥ መሆናቸው ከተገለጸው በሳዑዲ ከሚገኙ ኢትዮጵያዊ ስደተኞች መካከል 2 ሺዎቹን የመመለስ ሥራ ከአምስት ቀናት በኋላ እንደሚጀመር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ይፋ አደረገ።
ዘግይቶ እንቅስቃሴ የጀመረው የኢትዮጵያ መንግሥት 2 ሺኅ ስደተኛ ዜጎች ዝርዝር እንደተለየና የመመለሱም ሥራ ከጳጉሜ ሦስት- እስከ መስከረም 26 እንደሚተገበር ተሰምቷል።
መንግሥት በእስር ላይ ያሉ ኢትዮጵያውያንን ቅድሚያ በመስጠት የመመለስ ሥራውን እንደማጀምር ቢናገርም ኢትዮጵያውያኑ ለወራት ያሉበትን አስከፊ ሁኔታ በተመለከተ ዓለም ዐቀፍ ሚዲያዎችና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ሲገልጹ መሰንበቱ አይዘነጋም።
የኮሮና ቫይረስ ኢትዮጵያውያኑን ለመመለስ ፈታኝ እንደሆነበት የገለጸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፤ በዚህም ችግርም ውስጥ ተሁኖ 3 ሺኅ 500 የሚሆኑ ስደተኞችን በመመለስ በለይቶ ማቆያ ውስጥ እንዲገቡ፣ በኋላም ወደመጡበት ስፍራ የመላክ ሥራ መከናወኑን አብራርቷል።
ጉዳዮን አስመልክቶ የትግራይ ክልል ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር ደብረፅዮን ገብረ ሚካኤል ለሳዑዲ መንግሥት ከአንድ ወር በፊት በጻፉት ደብዳቤ ዜጎቹን ከሳዑዲ አረቢያ በአየር አንስቶ ወደ መቀሌ እንዲያደርስላቸው መጠየቃቸው ይታወሳል።
የኢትዮጵያና የሳዑዲ ከጥንት ጀምሮ ያላቸውን የተሳሳረ ታሪክ እንዲሁም በትግራይ ያለውን አል ነጃሺ መስጂድ ለዚህም ማሳያ መሆኑን በመጥቀስ ትብብር ያስፈልጋል ያለው የትግራይ ክልል መንግሥት ደብዳቤ በአሁኑ ወቅት ሳዑዲ ውስጥ በአስከፊ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙት የትግራይ ተወላጆች ናቸው ብሏል።
በተለይም በደርግ አገዛዝ ወቅት በርካታ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች መሸሻ አድርገው ሳዑዲ አረቢያን እንደቆዩና ከድህነት፣ ረሃብም ሆነ የተሻለ ኑሮን የፈለጉ በርካታ ኢትዮጵያውያን ሳዑዲ እንደ ሁለተኛ አገራቸው ሆና ቆይታለች ያለው የዶክተር ደብረፂይን የተማፅኖ ደብዳቤ፤
“የኢትዮጵያ የፌደራል መንግሥት ስደተኞቹን ለመቀበል ፈቃደኛ አይደለም፤ ክልሉ ግን ዜጎቹን ለመቀበል ፈቃደኛ ሆኖ እየተጠባበቀ ነው” ሲል መንግሥትን ክፉኛ ተችቷል።