በምስራቅ ጎጃም በደረሰ የመሬት መንሸራተት በርካታ መኖሪያ ቤቶች ደብዛቸው ጠፋ

በምስራቅ ጎጃም በደረሰ የመሬት መንሸራተት በርካታ መኖሪያ ቤቶች ደብዛቸው ጠፋ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በምስራቅ ጎጃም ዞን በአዋበል ወረዳ በሠባት ቀበሌዎች ያልተጠበቀ የመሬት መንሸራተት መድረሱ ተሰማ።

ተከሰተ በተባለው የመሬት መንሸራተት 135 ቤቶች ሲፈርሱ 336 አባወራዎች፣ በቤተሰብ ደረጃ  1ሺኅ 260 ሰዎች ለችግር መጋለጣቸው ተረጋግጧል።
ሚዛን፣ ጡረት፣ ለጋ የጠረብና፣ ጅት ባህር፣ ወጀል አንቅራቅ፣ እነቢ ጭፋር እና አዲስ አምባ ጨሊያ የተባሉት አካባቢዎች ሲሆን ጉዳቱ የደረሰው፤ የመሬት መንሸራተቱ ነሐሴ 22/2012 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 አካባቢ መከሰቱን እና በጊዜው ከ100 በላይ ቤቶች እንደፈረሱ ነዋሪዎች ይፋ አድርገዋል።
“አንዳንዶች ቤታችሁ የት ነው? ተብለው ሲጠየቁ ቤታቸው የት እንደሆነ፣ የት አካበቢ እንደሆነ ራሱ አያውቁትም” ያሉት የአካባቢው ነዋሪዎች፤ ቤቶቹ ከእነ ሙሉ ዕቃቸው መፍረሳቸውን እና አብዛኛዎቹ ነዋሪዎች ቤት ዘግተው ሥራ ላይ የነበሩ በመሆናቸው አደጋው አስከፊ ሊሆን መቻሉንም ገልጸዋል።
በአዋበል ወረዳ ሰባት ቀበሌዎች ከነሀሴ 22/2012 ጀምሮ የመሬት መንሸራተት መከሰቱን የወረዳው የአደጋ ቅድመ ማስጠንቀቂያ ምላሽ ቡድን መሪ አቶ አቶ አስማማው አሰፋ ተናግረዋል። የደረሰው ጉዳት ሙሉ ለሙሉ ተለይቶ ባይጠናቀቅም በመሬት መንሸራተቱ 336 አባወራዎች ጉዳት ሲደርስባቸው 135 ቤቶች ደግሞ መፍረሳቸውን አረጋግጠዋል።
በተጨማሪም ስልሳ የሚጠጉ ተጨማሪ ቤቶች የመፍረስ አደጋ የተደቀነባቸው መሆኑን፣ ከ125 እስከ 135 ሄክታር የሚደርስ መሬት ላይ ያለ ሰብል እና 135 ሔክታር ላይ ያለ አትክልትና ፍራፍሬ ላይ ጉዳት ከመድረሱ ባሻገር ከብቶች እና ፍየሎችም መሞታቸው ታውቋል።

LEAVE A REPLY