ትውልድ ለሰላም የተሰኘ ሀገር ዐቀፍ ንቅናቄ ዛሬ በይፋ ተጀመረ

ትውልድ ለሰላም የተሰኘ ሀገር ዐቀፍ ንቅናቄ ዛሬ በይፋ ተጀመረ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ትውልድ ለሰላም የተሰኘ ሃገር 0ቀፍ ዘመቻ ዛሬ በይፋ ተጀመረ። ዘመቻው “የኢትዮጵያ ህዝቦች ድምፅ ለሰላም” የሚል መጠሪያ እንደተሰጠውም ታውቋል።

ለዘመቻው ቅስቀሳ የሚሆነው በመላ ሃገሪቱ 1 ሚሊየን ፊርማ የማሰባሰብ ሥራ በዛሬው ዕለት የሰላም ሚንስትሯ ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል እና ታዋቂ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች፣ እንዲሁም ታዋቂ ግለሰቦች በተገኙበት መጀመሩ ተሰማ።
ቡድኑ ከቅስቀሳ ፊርማ ማሰባሰብ በተጨማሪ ተፅዕኖ ፈጣሪ ሰዎችና በሳል ተናጋሪዎች በተለያዩ መድረኮች የቅስቀሳ ንግግሮችን በማድረግ ሕብረተሰቡን በሰላም ዙሪያ የማነቃቃት ሥራ ይሠራል መባሉን ሰምተናል።
ፕሮግራሙ ኢትዮጵያዊያን የራሳቸውን ችግር በራሳቸው ተነጋግረው በመፍታት ለሰላማቸው ዘብ እንዲቆሙ ለማድረግ ነው ያለው መግለጫ፤ መተማመንና መከባበር ያለበት ማኅበረስብ ለመፍጠርም ታልሟል ብሏል።
የግጭቶችን መንስዔ ታሪካዊና ማኅበራዊ መነሻዎችን በማጥናትና በመለየት ኅብረተሰቡ ራሱ የለያቸው ችግሮች ከሲቪክ ማኅበራት ጋር በመነጋገር መፍትኄ እንዲያገኙ እንደሚደረግ ነው የተገለጸው።
 ” የኢትዮጵያ የሰላም ጉዳይ ድርብ ድርብርብ ችግር ያለበት፣ ለዘመናት የቆየ፣ ላለፉት አርባና ሀምሳ ዓመታት የፖለቲካ አካሄዳችን ዘመናዊነትን ባለመከተሉ የተፈጠረ ነው”  ያሉት የሰላም ሚኒስትሯ ሞፈሪያት ካሚል፤ “ሰላም የሚሠራ ሳይሆን የሚጠበቅ ስለሆነ ሰላምን የሚያደፈርሱ አሠራሮችን ካስወገድን፣ የሰለጠነ የፖለቲካ ባህል ከገነባንና ችግሮችን ተነጋግሮ መፍታት ከለመድን ለውጥ ማምጣት ይቻላል”  ሲሉ ተደምጠዋል።

LEAVE A REPLY