ሜቴክ የሕብረተሰቡን አመኔታ ሊያስገኝልኝ በሚችል መልኩ አደረጃጀቴን ለውጫለሁ አለ

ሜቴክ የሕብረተሰቡን አመኔታ ሊያስገኝልኝ በሚችል መልኩ አደረጃጀቴን ለውጫለሁ አለ

 ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በህወሓት መራሹ መንግሥት ከፍተኛ የሆነ ምዝበራና የሀብት ብክነት የተፈጸመበት የብረታ ብረት እና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) የቡድን አደረጃጀት በመጠቀም ራሱን በአዲስ መልክ ማደራጀቱን ገለጸ።
የጥቂት የማፍያ ቡድኖች መጠቂሚያ ሆኖ ለዓመታት የዘለቀው ሜቴክ ከዚህ ቀደም ካጠፋው ጥፋት አኳያ በቀጣይ የሕብረተሰቡን አመኔታ ለማግኘት በሚያስችለኝ አደረጃጀት ተዋቅሬ ወደ ሥራ ገብቻለሁ ብሏል።
ሜቴክ ባለፉት ጊዜያት በርካታ ክፍተቶች የነሩበት እና
ሀብት ሲባክንበት የነበረ ተቋም የነበረ ቢሆንም አሁን ግን የሠራተኞቹን አቅም በማጠናከር ተወዳዳሪ እና መሪ ለመሆን እየሠራ እንደሚገኝ በጅማሬው ማብሰሪያ ላይ ሰምተናል።
የብረታ ብረት እና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) ባለፉት ጊዜያት ካልተስተካከለ የፋይናንስ ሥርዓት ጀምሮ የሀብት አያያዝ እና የአደረጃጀት ችግር የነበረበት በመሆኑ በዚህ ምክንያት ቀላል የማይባል ንብረት መባከኑን የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ህይወት ሞሲሳ ተናግረዋል።
ተቋሙ ያለበትን ክፍተት እና ችግር በመለየት ምርት ሳይቆም እና ሠራተኛ ሳይበተን አሠራሩን ለማዘመን እና ለማሻሻል እየተሠራ ነው ያሉት ሥራ አስፈጻሚዋ፤
ተቋሙ የግሩፕ አደረጃጀት በመጠቀም ራሱን በአዲስ መልክ በመቀየር የህዝብ አመኔታ ለማግኘት እየሠራ ከመሆኑ ባሻገር ለሠራተኞቹም የአቅም ግንባታ ሥራ እና ተከታታይ ስልጠናዎችን እየሰጠ ነው ብለዋል።
የሜቴክ የቦርድ ሰብሳቢ የሆኑት ፕሮፌሰር ዳንኤል ቅጣው በበኩላቸው ፤ የብረታ ብረት እና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ዋነኛ ራዕይ መሪ እና አርአያ መሆን እና ሀገርን ከማሳደግ ባሻገር ተቋሙን ተወዳዳሪ ማድረግ እንደሆነ ገልጸዋል።

LEAVE A REPLY