ከ13 ዓመት በላይ የቆዮ 3 የኢትዮጵያውያን አትሌቶች ክብረ ወሰኖች ትናንት ተወሰዱ

ከ13 ዓመት በላይ የቆዮ 3 የኢትዮጵያውያን አትሌቶች ክብረ ወሰኖች ትናንት ተወሰዱ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በኢትዮጵያውያን አትሌቶች ተይዘው የነበሩ ሁለት  ክብረ ወሰኖች (የዓለም ሪከርድ)  በትናንቱ የዳይመንድ ሊግ ውድድሮች መሰባበራቸው ታወቀ።

ትውልደ ሶማሊያዊው ሞ ፋራህ በኃይሌ ገብረ ሥላሤ ለ13 ዓመታት ተይዞ የነበረውን ክብረ ወሰን አሻሽሎታል።
ለእንግሊዝ የሚሮጠው የአራት ጊዜ የኦሎምፒክ ሻምፒዮኑ ሞ ፋራህ የአንድ ሰዐት የዓለም ክብረ ወሰንን በዳይመንድ ሊግ ውድድር ላይ ትናንት ምሽት ማሻሻል ችሏል።
ሞ ፋራህ በአንድ ሰዐት ውስጥ 23.33 ኪሎ ሜትር በመሮጥ የሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሤን 21.285 ኪሎ ሜትር ርቀት ከ13 ዓመት በኋላ እንዳዳሻሻለው መረጃዎች ያሳያሉ።
“የዓለም ክብረ ወሰንን መስበር ቀላል ነገር አይደለም። ይህን ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ። ይህ ክብረ ወሰን ለረዥም ጊዜ ሳይሰበር ቆይቷል” ያለው ሞ ፋራህ ውድድሩም ሆነ ዝግጅቱ ከባድ እንደነበር ጠቁሟል።
ይህ  ውድድር አትሌቶች በአንድ ሰዐት ውስጥ በተቻላቸው መጠን ረዥም ርቀትን ለመሸፈን የሚወዳደሩበት ነው።
ከዚህ የሞ ፋራህ ውጤት ቀደም ብሎ በተካሄደ ተመሳሳይ የሴቶች ውድድርም ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ሲፈን ሃሰን በተመሳሳይ የዓለም ክብረ ወሰንን ማሻሻል ችላለች።
ለኔዘርላንድ የምትሮጠው ሲፈን  ያሻሻለችው ክብረ ወሰን በኢትዮጵያዊቷ አትሌት ድሬ ቱኔ ተይዞ የነበረ ነው።
ሲፈን በአንድ ሰዐት ውስጥ 18.930 ኪሎ ሜትር በመሮጥ ከ14 ዓመታት በፊት ድሬ ቱኔ አስመዝግባ የነበረውን 18.517 ኪሎ ሜትር ማሻሻል ችላለች።
በ15 ዓመቷ ወደ ኔዘርላንድ የሄደችውና ዜግነቷን የቀየረችው ሲፈን ሀሰን በያዝነው ዓመት ከቢቢሲ ጋር በነበራት ቃለመጠይቅ ላይ “ለኢትዮጵያ ለመሮጥ ታስቢያለሽ ወይ?” በሚል ለቀረበላት ጥያቄ፤ “ለኢትዮጵያ አልሮጥም፣ የኦሮሞ ጥያቄ ከተመለሰ ግን ለኦሮሚያ ብሮጥ ደስ ይለኛል” የሚል ምላሽ መስጠቷ አይዘነጋም።

LEAVE A REPLY