በኢትዮጵያ የባንክ ኢንዱስትሪው ችግር ቢኖርበትም እያደገ ነው ተባለ

በኢትዮጵያ የባንክ ኢንዱስትሪው ችግር ቢኖርበትም እያደገ ነው ተባለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በኢትዮጵያ የባንክ ኢንዱስትሪው እያደገ እንደሆነ የባንኮች ብዛት ማሳያ ነው ተባለ።

በአሁኑ ሰዐት በሃገሪቱ 18 ባንኮች ሥራ ላይ መሆናቸው የተነገረ ሲሆን፤ 5 የሚሆኑ ደግሞ ገበያውን ለመቀላቀል እየተንደረደሩ መሆናቸው ታውቋል።
በዚህን ያህል ደረጃ ባንኮች በኢትዮጵያ እየተስፋፉ ቢሆንም  ባንኮቹ አዳዲስ አሠራሮችን በማስተዋወቅ ረገድ የሚጠበቀውን ያህል አይደሉም በሚል በዘርፉ ባለሙያዎች እየተተቹ ይገኛል።
ደንበኛን ለመሳብና ለማብዛ፣ ብድር ለመስጠትም ሆነ ሌሎች መሰል አገልግሎቶችን ለማቅረብ የሚጠቀሙባቸው ስልቶች ውስን የሕብረተሰብ ክፍልን ብቻ ትኩረት ያደረጉ ናቸው የሚል ጥናቶችም በባለሙያዎቹ ተገኝተዋል።
ባለሙያዎቹ ከዚሁ ጎን ለጎን እስካሁን ያሉበት አዝጋሚ የፉክክር ሜዳ የሚለወጥበት ጊዜና ሁኔታዎች ወደ የባንኮቹ ደጃፍ እየቀረቡ እንደሆነ እየታየ መሆኑንም ይናገራሉ።
ባንኮቹ ነባራዊ ሁኔታውን ተገንዝበው ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን የሚደርስ አውድ ላይ ከሠሩ ደግሞ የበለጠ በዘርፉ የተሻለ ውጤትና እድገት ማስመዝገብ ይቻላል ተብሏል።

LEAVE A REPLY