አድማስ ዮኒቨርስቲ 850 የድኅረ ምረቃ ተማሪዎቼን ኮሮናን ተቋቁሜ አስመርቂያለሁ አለ

አድማስ ዮኒቨርስቲ 850 የድኅረ ምረቃ ተማሪዎቼን ኮሮናን ተቋቁሜ አስመርቂያለሁ አለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– አድማስ ዩኒቨርሲቲ በአዲስ አበባ ካምፓሶቹ በተለያዩ የትምርት ዘርፍ ያሰለጠናቸውን 850 የድህረ ምረቃ ተማሪዎችን ዛሬ አስመረቀ።

የኮሮና ቫይረስ የፈጠረው ተፅዕኖ የገፅ ለገፅ ትምህርቱ እንዲቋረጥ ምክንያት ቢሆንም ዩኒቨርሲቲው ተፅዕኖውን በመቋቋም አዲስ አበባ በሚገኙ ካምፓሶቹ 850 የድህረ ምረቃ ተማሪዎችን በበይነ መረብ ትምህርታቸው እንዲቀጥሉ አስችያለሁ ብሏል።
የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳት ዶክተር ሞላ ፀጋይ ተማሪዎቹ ትምህርታቸውን በበይነመረብ እንዲከታተሉ ለማስቻል ብዙ መሰናክሎች ቢኖሩም፣ ባለው ቴክኖሎጂ ቁጥጥር ተደርጎ ተማሪዎቹን ለማስመረቅ መቻላቸውን ጠቁመው፤
 ከዚህ በተጨማሪ ተማሪዎች በይነ መረብን በዘላቂነት እንዲጠቀሙ ለማድረግ ዮንቨርስቲው ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ ይገኛል ብለዋል።
በምረቃ ሥነ-ሥነሥርዓቱ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሙሉ ነጋ እስካሁን በከፍተኛ ትምህርት ተደራሽነት ፍትሃዊ ውጤት ቢመዘገብም ፤ በትምህርት ጥራትና አግባብነት ላይ ቀሪ ነገሮች በመኖራቸው ካለፉት ድክመቶችና ውጤቶች በመንተራስ የሪፎርም ሥራ እየተካሄደ ነው ብለዋል።

LEAVE A REPLY