የወ/ሮ አዳነች አቤቤ ይቅርታ ግልጽ አይደለም ተባለ

የወ/ሮ አዳነች አቤቤ ይቅርታ ግልጽ አይደለም ተባለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ጳጉሜን 1 የይቅርታ ቀን ነው መባሉን ተከትሎ  በአዲስ አበባ ከተማ የተለያዩ ዝግጅቶች እየተከናወነ ይገኛል።

ዛሬ ማለዳ ከ12፡00 ጀምሮ የመንገድ ዳር ብረቶችንና የከተማዋ ዋና ዋና መንገዶችን ኬሚካል የመርጨት ሥራ ወጣቶች አካሂደዋል።
እነዚህ ወጣቶች  የአባቶችን እግር በማጠብ ከአባቶች ምርቃት የተቀበሉበት ፕሮግራም መከናወኑም ተነግሯል።
የይቅርታ ቀንን በይፋ ያስጀመሩትና በመስቀል አደባባይ በመገኘት የመንገድ ዳር ብረቶችን የማጽዳት እና ኬሚካል የመርጨት ሥራ ያከናወኑት የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ፤ አካባቢያችንን ከተህዋሲያንና ከቆሻሻ በማጽዳት ኮሮና ቫይረስን መከላከል ይቻላል ሲሉ ተደምጠዋል።
“እንደ ቆሻሻው ሁሉ ውስጣችንን ከጥላቻ፣ ከቂም በቀልና ከመራራቅ ይልቅ አዲሱን ዓመት በይቅርታ ልንቀበል ይገባል   ያሉት አዲሷ ከንቲባ፤ መጪው 2013 ዓ.ም አዲሱ ዓመትን በይቅርታ፣ በአብሮነትና በመተሳሰብ እንዘልቃለን ከማለታቸው ባሻገር፣ “የከተማችን ነዋሪዎች በአካልም በመንፈስም ከሚያራርቀው ጥላቻ ተላቅቀው በህብረት ለመሻገር ይቅርታ ሊደራረጉ ይገባዋል” የሚል መልእክት አስተላልፈዋል።
ይቅርታው ከዚህ በፊት በሓላፊነት ይሰሩበት ለነበረው ጉምሩክ ወይንም አቃቤ ሕግ መስሪያቤት የሚነሳባቸውን ክስ አስመልክተው ይሁን ወይንስ አሁን ለተመደቡበት አዲስ አበባ የተገለጸ ነገር የለም።

LEAVE A REPLY