ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– የኮሮና ቫይረስ ሥርጭትን ለመግታት ወጥቶ የነበረው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መነሳትን ተከትሎ ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ ይደረጉ የነበሩ ጥንቃቄዎች ሊረሱ ይችላል የሚል ስጋት መኖሩ ተሰማ።
ከመደበኛ ጥንቃቄዎች በተለየ መልኩ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማብቃቱን ተከትሎ በአስከሬን አያያዝ እና የቀብር ሥነ-ሥርዓት ላይ የነበረው ጥንቃቄ እንዳይጓደል ስለምሰጋ አስፈላጊው ጥንቃቄ ይደረግ ያለው የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ነው።
በመሆኑም ኅብረተሰቡ በመንግሥትና በጤና ተቋማት የቫይረሱን ሥርጭት መቆጣጠር ተችሏል የሚል መግለጫ እስኪሰጥ ድረስ በየትኛውም ሁኔታ ሕይወታቸው ያለፈ ሰዎችን አስከሬን ማስመርመር አሁንም ግዴታ መሆኑን መርሳት የለበትም ተብሏል።