በአዲስ አበባ ትራንስፖርት አገልግሎት ታሪፍና የመጫን አቅም መመሪያ ላይ ማሻሻያ ተደረገበት

በአዲስ አበባ ትራንስፖርት አገልግሎት ታሪፍና የመጫን አቅም መመሪያ ላይ ማሻሻያ ተደረገበት

ADDIS ABABA, ETHIOPIA - APRIL 4 : Ethiopian Transport Minister Dagmawit Moges speaks during a press conference on "Boeing 737 Max 8" crash in Addis Ababa, Ethiopia on April 4, 2019. (Photo by Minasse Wondimu Hailu/Anadolu Agency/Getty Images)

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– የኮሮና ቫይረስን ሥርጭት ለመግታት ሲባል በአዲስ አበባ  በወጣው የትራንስፖርት አገልግሎት ታሪፍና የመጫን አቅም መመሪያ ላይ ማሻሻያ መደረጉ ተነገረ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ባለሥልጣን  የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ሚኒባስ፣ የአንበሳ አውቶብስ፣ ሸገር እና ሀይገር ባሶች በወንበራቸው ልክ እንዲጭኑ ተወስኗል ብሏል።
የሚኒባስ ታክሲዎች ከኋላ ባለው መቀመጫ ከ2 ሰው በላይ መጫን አይችሉም ያለው ቢሮው ፤
እንዲሁም ባለ ሦስት እና ባለ አራት እግር (ባጃጅ) ተሽከርካሪዎች እስከ ሹፌሩ 3 ሰው መጫን እንደሚችሉም አብራርቷል።
ቀላል ባቡር በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መመሪያ በ25 በመቶ የመጫን አቅም ብቻ አገልግሎት ሲሰጥ የነበረ ቢሆንም አሁን ላይ ወደ 75 በመቶ ክፍ እንዲል መደረጉን የጠቆመው መግለጫ፤ ከታሪፍ ጋር በተያያዘም በእጥፍ ሲከፈል የነበረው ቀርቶ መጠነኛ ማሻሻያዎች መደረጋቸውን ይፋ አድርጎል።
በወጣው መመሪያ መሰረት የሚኒባስ ታክሲ ታሪፍ ፦
* እስከ 2 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር ፣ በፊት 1 ከ50 ሳንቲም የነበረው አሁን ላይ 2 ብር
* ከ2 ነጥብ 6 እስከ 5 ኪሎ ሜትር በፊት 3 ብር የነበረው አሁን 4 ብር
* ከ5 ነጥብ 1 እስከ 7 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር በፊት 4 ብር ከ50 ሳንቲም የነበረው አሁን 6 ብር
* ከ7 ነጥብ 6 እስከ 10 ኪሎ ሜትር በፊት 6 ብር የበረው አሁን 8 ብር
* ከ10 ነጥብ 1 እስከ 12 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር 7 ብር ከ50 ሳንቲም የነበረው አሁን 10 ብር
* ከ12 ነጥብ 6 እስከ 15 ኪሎ ሜትር በፊት 9 ብር የነበረው አሁን 12 ብር
* ከ15 ነጥብ 1 እስከ 17 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር በፊት 10 ብር ከ50 ሳንቲም የነበረው አሁን 13 ብር
* ከ17 ነጥብ 6 እስከ 20 ኪሎ ሜትር በፊት 12 ብር የነበረው አሁን 15 ብር
* ከ20 ነጥብ 1 እስከ 22 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር በፊት 13 ብር ከ50 ሳንቲም የነበረው አሁን 17 ብር
* ከ22 ነጥብ 6 እስከ 25 ኪሎ ሜትር በፊት 15 ብር የነበረው አሁን 19 ብር
* ከ25 ነጥብ 1 እስከ እስከ 27 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር በፊት 16 ብር ከ50 ሳንቲም የነበረው አሁን 20 ብር
* ከ27 ነጥብ 6 እስከ 30 ኪሎ ሜትር በፊት 18 የነበረው አሁን 22 ብር ሆኖ ማሻሻያ ተደርጎበታል።
ከተፈቀደው ሰው በላይ መጫን ከ1 ሺኅ ብር ጀምሮ ከታሪፍ በላይ ማስከፈል 1 ሺህ 500 ብር ጀምሮ እንደሚያስቀጣ የገለጸው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ባለሥልጣን ይህን በአግባቡ ለመተግበር ኅብረተሰቡም አስፈላጊውን ትብብር ሊያደርግ ይገባል ብሏል።

LEAVE A REPLY