የኢትዮጵያ ልጆች ቲቪ መሥራች፣ ቤታቸውን ለመጠለያ የሰጡና 100 ጊዜ ቦንድ የገዙ ግለሰብ...

የኢትዮጵያ ልጆች ቲቪ መሥራች፣ ቤታቸውን ለመጠለያ የሰጡና 100 ጊዜ ቦንድ የገዙ ግለሰብ የዓመቱ በጎ ሰው ተባሉ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ባለፉት አምስት ወራት በኢትዮጵያ የተከሰተውን የኮቪድ 19 ኮሮና ቫይረስ ሥርጭት ለመግታት በሚደረገው ጥረት ውስጥ የገዛ መኖሪያ ግቢያቸውን ሳይቀር በመስጠት፣ መጠለያ የሌላቸውን በመደገፍ ረገድ የበጎ አድራጎት ሥራ የሠሩት ካሊድ ናስር በ8ኛው የበጎ ሰው ሽልማት ድርጅት ልዩ ተሸላሚ ሆነዋል።
ከእርሳቸው በመቀጠል በሁለተኛነት ልዩ ተሸላሚ የሆኑት ኪሮስ አስፋው የተባሉት ግለሰብም ከህዳሴ ግድብ ግንባታ ጋር በተያያዘ ባደረጉት በጎ ሥራ የተሸለሙ ሲሆን፤ ላለፉት ዘጠኝ ዓመታት ያለማቋረጥ መቶ ጊዜ ቦንድ የገዙ መሆናቸው ይፋ ተደርጓል።
የንባብ ለሕይወት መሥራችና አዘጋጆች መካከል የሚገኘው ጋዜጠኛ ቢንያም ከበደ የ8 ኛው በጎ ሰው ሽልማት ልዩ ተሸላሚ ሆኖ ተመልክተነዋል። ቢንያምን ለሽልማት ያበቃው በኮቪድ 19 ወቅት ልጆች በየቤታቸው ሲሆኑ የሚመለከቱት፣ የሚመጥናቸውና ፕሮግራም ብቻ በተለያየ ቋንቋ መሰናዶዎች የሚቀርብበት “የኢትዮጵያ ልጆች” ቴሌቭዥንን መክፈቱ እንደሆነም ታውቋል።

LEAVE A REPLY