ልደቱ አያሌው ላይ ያልተፈቀደ የጦር መሣሪያ ይዞ በመገኘት ክስ ተመሠረተባቸው

ልደቱ አያሌው ላይ ያልተፈቀደ የጦር መሣሪያ ይዞ በመገኘት ክስ ተመሠረተባቸው

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– የቀድሞው የቅንጅትና ኢዴፓ ከፍተኛ አመራር የነበሩት አቶ ልደቱ አያሌው የጦር መሳሪያ አስተዳደር አዋጅ 1177/2012 አንቀጽ 22 ንዑስ አንቀጽ ሦስትን በመተላለፍ፣ ያልተፈቀደ የጦር መሳሪያ ይዞ በመገኘት ወንጀል ክስ እንደቀረበባቸው ታወቀ።

ክሱ አሁን ታስረው በሚገኙበት ቢሾፍቱ ከተማ በምስራቅ ሸዋ ዞን ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ የቀረበባቸው ሲሆን፤ በዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤትም  ክስ ተመስርቶባቸዋል ፡፡
ከምርጫ 97 የቅንጅት መፈራረስ በኋላ በበርካታ ኢትዮጵያውያን ዘንድ በከሃዲነት የተፈረጁት ልደቱ፤ ከዚህ በፊት በሰኔ 23 እና 24 በቢሾፍቱ ከተማ አመጽና ሁከት እንዲቀሰቀስ፣ በገንዘብ ሲደግፉና ሲያስተባብሩ ነበር ተብለው ምርምራ ሲከናወንባቸው መቆየቱ አይዘነጋም።
ዐቃቤ ህግ በዚህ ምርመራ ላይ ፍቃድ የሌላቸው የጦር መሳሪያ አግኝቼባቸዋለሁ በማለት ፤ ህገወጥ የጦር መሳሪያ ይዞ መገኘት ወንጀል ክስ አቅርቦባቸዋል።

LEAVE A REPLY