ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– ባለፉት 24 ሰዐታት ውስጥ ለ8 ሺኅ 221 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 602 ሰዎች ኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር ገለጸ።
በኢትዮጵያ በአጠቃላይ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 67 ሺህ 515 መድረሱን የጠቆመው መግለጫ፤ በትናንትናው ዕለት 553 ሰዎች ከበሽታው ማገገማቸውን ተከትሎ በአጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 27 ሺኅ 638 ደርሷል ብሏል።
በአንጻሩ ባለፉት 24 ሰዐታት በኮሮና ቫይረስ የ12 ሰዎች ህይወት ማለፉ መረጋገጡን ተከትሎ፣ በበሽታው የሞቱ ሰዎች ቁጥር 1 ሺኅ 72 መግባቱን ለማወቅ ተችሏል።
በአሁኑ ወቅት ቫይረሱ ካለባቸው 38 ሺኅ 803 ሰዎች መካከል 289 ያህሉ በጽኑ ሕክምና ላይ መሆናቸውንም ሚኒስቴሩ ይፋ አድርጓል።
የኮሮና ቫይረስ ስርጭት በኢትዮጵያ እየተስፋፋ ቢሆንም መንግሥት የትራንስፖርት አገልግሎትን ወደ ቀደመ የሰው ጭነት ልክ ከመመለስ ባሻገር የተለያዮ ገደቦችን በማንሳት ትምህርት ለመጀመርና ምርጫ ለማካሄድ ሽር ጉድ መጀመሩ ከወዲሁ በርካታ የሃገሪቱን ዜጎች እያነጋገረ ይገኛል።