በድንበር አካባቢ የሚከሰቱ ግጭቶች ዙሪያ መንግሥት እርምጃ እንደሚወስድ ዶክተር ዐቢይ አስታወቁ

በድንበር አካባቢ የሚከሰቱ ግጭቶች ዙሪያ መንግሥት እርምጃ እንደሚወስድ ዶክተር ዐቢይ አስታወቁ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– የፌደራል እና የክልል መንግሥታት አመራሮች የሀገሪቱን በርካታ ክልሎች ያጠቃውን የተፈጥሮ አደጋ አስመልክቶ መንግሥት የወሰዳቸውን ርምጃዎች መገምገማቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስታወቁ።

ከፍተኛ የጎርፍ መጥለቅለቅ ቢከሠትም፣ ምንም ዓይነት የሞት አደጋ አለመድረሱ መልካም ነው በማለት የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ የሀገር መከላከያ ሠራዊት በየስፍራው ተገኝቶ አስፈላጊውን ድጋፍ እየሰጠ ይገኛል ብለዋል።
“በተደጋጋሚ ባደረግናቸው ውይይቶች በሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት የሚከናወኑ እርዳታዎችን ጨምሮ፣ በበርካታ ጉዳዮች ላይ ቀጣይ አቅጣጫን አስቀምጠናል” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፤ አልፎ ፣ አልፎ የሚነሡትና የዜጎች ሕይወትና ንብረት እየነጠቁ ያሉትን የጸጥታ እክሎችን በተመለከተም ተገቢው ውይይቶች መካሄዳቸውን በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ባሰፈሩት ጽሑፍ አመላክተዋል።
 በድንበር አካባቢ የሚፈጠሩት ክሥተቶች፣ የለውጡን ጉዞ ለማደናቀፍ በሚሹ ቡድኖች የሚቀናበሩ መሆናቸውን ያመላከተው የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽሑፍ፤ በእነዚህ ግጭቶች ውስጥ ተሳታፊ የሆኑትን ሁሉ በሕግ ተጠያቂ ለማድረግ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የሚመራው ቡድን ሥራውን በአግባቡ እየሠራ ነው ሲል ያሳያል።

LEAVE A REPLY