ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ አስቸኳይ ስብሰባ ነገ እንደሚያካሂድ ተነገረ።
የምክር ቤቱ በአስቸኳይ ስብሰባው ሁለት አጀንዳዎች ላይ ይመክራል ነው የተባለው። በቀዳሚነትም የምክር ቤቱን 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ አስቸኳይ ስብሰባ ቃለ ጉባኤ መርምሮ የሚያፀድቅ ሲሆን፤ በመቀጠልም የጤና ሚኒስቴር ሃገራዊ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምላሽና ቀጣይ እርምጃዎች በተመለከተ በሚያቀርበው ሪፖርት ላይ ተወያይቶ ውሳኔ እንደሚያሳልፍ ይጠበቃል።
ፓርላማው ነገ ከሚያካሂደው አስቸኳይ ስብሰባ በተጨማሪ የፊታችን ሰኞ መስከረም 11 ቀን 2013 ዓ ም አስቸኳይ ስብሰባ የሚያደርግ መሆኑንም ለማወቅ ተችሏል።