አዳነች አቤቤ የሆራ ፊንፊኔ ማክበሪያ ቋሚ ቦታ ማረጋገጫ ለአባገዳዎች መስጠታቸው አነጋጋሪ ሆነ

አዳነች አቤቤ የሆራ ፊንፊኔ ማክበሪያ ቋሚ ቦታ ማረጋገጫ ለአባገዳዎች መስጠታቸው አነጋጋሪ ሆነ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ታሪክ ለሁለተኛ ጊዜ በአዲስ አበባ ከተማ ይከበራል ለሚባለው  ለሆራ ፊንፊኔ የኢሬቻ በዓል ማክበሪያ ስፍራ የከንቲባ አዳነች አቤቤ አስተዳደር የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ለአባገዳዎች ማስረከቡ ተሰማ።

ዋዜማው የሚከበርለት ብቸኛው በዓል (ብዙዎች ከበዓሉ ውጭ እንደሆነ ይናገራሉ) የኢሬቻ በአል በዚህ ዓመት በአዲስ አበባ ከተማ መስከረም 23 ቀን ይከበራል ተብሎለታል።
ይህንን ተከትሎም በቅርብ የመዲናዋ ምክትል ከንቲባ ሆነው በተሾሙት ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የሚመራው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር  ለሆራ ፊንፊኔ የኢሬቻ በዓል ማክበሪያ ስፍራ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ለአባገዳዎች ዛሬ በይፋ መስጠቱ ከወዲሁ ግርምትን ፈጥሯል።
ካርታውን ያስረከቡት የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ  አዳነች አቤቤ፤ ስፍራው የቀደመ የኢሬቻ በዓል የሚከበርበት ቦታ መሆኑ በመረጋገጡ የማረጋገጫ ሰነድ መሰጠቱ ግድ ነው ማለታቸው ደግሞ የኢሬቻ በዓል “ዋዜማ” ተብሎለት በከተማዋ በይፋ ተከብሮ እንደማያውቅ ጠንቅቀው የሚያውቁ ኗሪዎችን ከፌደራል መንግሥቱ እስከ ከተማው ባለሥልጣናት ድረስ “የፊንፊኔ ኬኛ” እና የተረኝነት ፖለቲካ በግልጽ እየተደገፈ ነው ሲሉ ቅሬታቸውን በተለያዮ ማኅበራዊ ሚዲያዎች እየገለጹ ይገኛሉ።
የኦሮሚያ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሓላፊ ከበደ ዴሲሳ በበኩላቸው አስተዳደሩ እሴቱ እንዲጎለብት፣ ለበዓሉ ቋሚ ማበክበሪያ ቦታ የማረጋገጫ ሰነድ በመስጠቱ እናመሰግናለን ብሏል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህዝቡን ጥያቄ በመመለሱ ምስጋናቸውን ያቀረቡት አባገዳዎችም የዘንድሮ የኢሬቻ በዓል አከባበር በአዲስ አበባ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት በተወሰኑ ሰዎችን እናከብራለን ሲሉ ተደምጠዋል።

LEAVE A REPLY