148 ኢትዮጵያውያን ከሊባኖስ ወደ ኢትዮጵያ መመለሳቸው ታወቀ

148 ኢትዮጵያውያን ከሊባኖስ ወደ ኢትዮጵያ መመለሳቸው ታወቀ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በሊባኖስ ይኖሩ የነበሩ ተጨማሪ 28 ኢትዮጵያውያን ዛሬ መስከረም 8 ቀን 2013 ዓ.ም. ጧት ወደ ሃገር ቤት መመለሳቸው ተሰማ።

በአጠቃላይ 148 ኢትዮጵያውያን ዛሬ፣ ትናንትና፣ ባለፉት ቀናት ወደ ሃገር ቤት መግባታቸው ታውቋል። ከስደት ተመላሾቹ የጉዞ ሰነዶች ያልነበራቸው ሲሆኑ፣ በቆንስላው በኩል የጉዞ ሰነዶች እና የመውጫ ቪዛ ተሠርቶላቸው የተመለሱ ናቸው፡፡
ኢትዮጵያውያኑ በሊባኖስ እስር ቤቶች የነበሩ፣ ሆስፒታል ሕክምናቸውን ሲከታተሉ የነበሩ፣ በቤሩት ወደብ ፍንዳታ መጠለያ ያጡና ችግር ላይ የነበሩ፤ እንዲሁም በአሠሪዎች በደልና የመብት ጥሰቶች፣ የአካልና የስነ-ልቦና ጉዳት የደረሰባቸው እና መጠለያና ምግብ ያጡ የነበሩ መሆናቸው ተነግሯል።
 ወደ ሃገራቸው መመለስ የሚፈልጉ ሆኖም ግን ምንም አይነት የጉዞ ሰነዶችና ፓስፖርት የሌላቸውን ኢትዮጵያውያን መመለስ እንዲችሉ የጉዞ ሰነድና የመውጫ ቪዛዎችን እንዲያገኙ የማድረጉን ሥራ ቆንስላ ጀነራል ጽ/ቤቱ ትኩረት ሰጥቶ እየተሠራበት መሆኑንም ይፋ አደርጓል።

LEAVE A REPLY