ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ከሠባት ወራት በኋላ በኢትዮጵያ ትምህርት ሲጀመር የትምህርት አሳጣጥ ሂደቱ በፈረቃ እንደሚሆን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።
በፈረቃ የሚሰጠው ትምህርት እንደ የአካባቢው ሁኔታ ከ2 እስከ 3 ፈረቃ ተከፍሎ ሊሰጥ እንደሚችልም የሚኒስቴር መ/ቤቱ መግለጫ ያሳያል።
የ2013 ዓ.ም የመማር ማስተማር ሥራው በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች እንደሚጀመርም የትምህሶት ሚኒስትር ይፋ አድርጓል።
በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ለሠባት ወራት ተቋርጦ የቆየው መደበኛ ትምህርት አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ ዳግም ለማስጀመር አስፈላጊው ዝግጅት ተጠናቋልጰነው የተባለው።
መንግሥት በትምህርት ቤቶች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ፣ ውሃ እና የእጅ ማጽጃዎችን በማሟላት፣ እንዲሁም ትምህርት ቤቶችን በማጽዳት መደበኛው ትምህርት እንደሚጀመር ከወዲሁ አረጋግጧል።