ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባዔ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ለመጀመሪያ ጊዜ በርቀት በቪዲዮ ኮንፍረንሲንግ መላ ዛሬ ይከፈታል።
የዘንድሮው 75ኛው ጠቅላላ ጉባዔ ሲሆን፤ በቀደሙት ዓመታት የሃገራት እና የመንግሥታት መሪዎች ለዚሁ ጉባዔ ዝግጅታቸውን አጠናቀዋል።
በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት በቪዲዮ ኮንፍረንሲንግ በርቀት ለመካሄድ በተገደደው ጉባዔ፤ ወረርሽኙን በጋራ መከላከል በሚቻልበት ጉዳይ መልዕክቶች እንደሚተላለፉበት እየተነገረ ነው።
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቀደም ሲል የተረጋገጠ የኮሮና ቫይረስ መከላከያ ክትባት ሲገኝ ለድሆቹም አገሮች ለማዳረስ የ10.3 ቢሊዮን ዶላር የእርዳታ ጥሪ ማቅረቡ አይዘነጋም።