አንበሳ አውቶቢስ ዋና መሥሪያ ቤቱን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ተነጠቀ

አንበሳ አውቶቢስ ዋና መሥሪያ ቤቱን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ተነጠቀ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና|| እድሜ ጠገቡ አንበሳ አውቶቢስ ለበርካታ ዓመታት ሲገለገልበት የኖረውን ዋና መሥሪያ ቤቱን በከተማ አስተዳደሩ ተነጠቀ።

እንደ ታማኝ ምንጮች ገለጻ ከሆነ አንበሳ የከተማ ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት ከምስረታው ጀምሮ ይጠቀምበት የነበረውን ዋና መሥሪያ ቤት ለመልቀቅ  የተገደደው በአዳነች አቤቤ በከተማ አስተዳደር ትዕዛዝ ነው።
በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 በተለምዶ አንበሳ ጋራዥ በመባል የሚታወቀውን የድርጅቱን ዋና መሥሪያ ቤት ለመልቀቅ የተገደደው፤ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቦታው ለግንባታ ይፈለጋል በሚል ነው።
በገርጂ አካባቢ የሚገኘው ይህ የአንበሳ አውቶቢስ ዋና መሥሪያ ቤት፤ ለጊዜው ምን እንደሆነ ላልታወቀ ግንባታ ይፈለጋል በሚል ድፍን ያለ ትዕዛዝ እንዲፈርስ መወሰኑን፣ የከተማ ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት የብዙኃን ትራንስፖርት ስምሪት ቁጥጥር ዋና የሥራ ሂደት መሪ የሆኑት መላኩ ካሳ ደስታ ለተለያዮ ሚዲያዎች ይህንን ጉዳይ አስመልክቶ ሲገልጹ ተደምጠዋል።

LEAVE A REPLY