ኢትዮጵያ ነገ ዜና|| የኢትዮጵያ አየር መንገድ አገልግሎቱን ሙሉ በሙሉ ከንክኪ ነፃ በሚያደርግው መተግበሪያ አማካኝነት መስጠቱ የደንበኞቹን እርካታ ጨምሯል ተባለ።
አየር መንገዱ አሠራሮቹን ሙሉ በሙሉ ከንክኪ ነፃ በማድረግ የዲጅታል ሥራዉን እያሳደገ እንደሚገኝ በአየር መንገዱ የዲጅታል ሽያጭና ግብይት ሥራ አስፈፃሚ አቶ ሱራፌል ወርቁ ገልጸዋል።
የአሠራሩ ዘመናዊነት የአየር መንገዱን ደንበኞች እርካታ እንዲጨምር አድርጓል ያሉት አቶ ሱራፌል፣ 1 ነጥብ 1 ሚሊዮን የአየር መንገዱ ደንበኞች በመተግበሪያው በኩል አገልግሎቱን እያገኙ ነው ብለዋል።
መተግበሪው 12 የሃገር ውስጥ እና የውጭ ቋንቋዎች እንዳለው የጠቆሙት በኢትዮጵያ አየር መንገድ የተንቀሳቃሽ ስልክ መተግበሪያ ምርት ስፈሥራ አስፈጻሚ ትዕግስት ስለሺ፣ ሦስት ዓመት በሆነው መተግበሪያ ላይ አዳዲስ አገልግሎቶችን በመጨመር፣ ተገልጋዮች ያለ ጊዜ ገደብ ሙሉ ለሙሉ ከንክኪ ውጭ የሆነ አገልግሎት እንዲያገኙ ያስችላል ሲሉ ተደምጠዋል።
በአፍሪካ ግዙፉና በዓለም ዐቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአገልግሎት አሰጣጡን በየጊዜው እያዘመነ ሲሆን፤ ባለፈው ሳምንት በፎርብስ መጽሔት፣ በሲምፕል ፍላይንግ ፣ እንዲሁም በሰኔ ወር በብሉምበርግ የኮሮና ወረርሽኝን ተፅዕኖ ተቋቁሞ ያተረፈ አየር መንገድ መባሉ ይታወሳል።