ፓርላማው ሃገራዊ ምርጫው እንዲካሄድና ትምህርት እንዲጀመር ዛሬ ወሰነ

ፓርላማው ሃገራዊ ምርጫው እንዲካሄድና ትምህርት እንዲጀመር ዛሬ ወሰነ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና||  በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ተራዝሞ የነበረው ሥድሥተኛው ሃገራዊ ምርጫ እንዲካሄድ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ወሰነ።

ምክር ቤቱ በ5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ አስቸኳይ ስብሰባ፤ ቀጣዮና ለ6ኛ ጊዜ የሚካሄደው ጠቅላላ ሃገራዊ ምርጫ የዓለም ጤና ድርጅትና የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ባስቀመጡት ምክረ ሃሳብ መሰረት፣ ቫይረሱን ለመካላከል የሚያስችሉ እርምጃዎችን በመውሰድ እንዲከናወን ተወስኗል።
 የውሳኔ ሀሳቡ በአንድ ተቃውሞና በስምንት ድምፀ ተዐቅቦ በአብላጫ ድምፅ ፀድቋል። በተጨማሪም ምክር ቤቱ ከኮሮና ቫይረስ መከሰት በኋላ የበሽታውን መስፋፋት ለመቆጣጠር በሚል ተከልክለው የነበሩ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች እንዲጀመሩ፣ እንዲሁም ተዘግተው የከረሙ ትምህርት ቤቶችም ይከፈቱ ሲል ወስኗል።
የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ምላሽ አሰጣጥና ቀጣይ እርምጃዎችን በተመለከተ ምክር ቤቱ መስከረም 8 ቀን 2013 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ፤ ምርጫው ከጥንቃቄ ጋር መደረግ ይችላል የሚል ምክረ ሀሳብ በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በኩል ቀርቦለት እንደነበርም ተሰምቷል።
ይህ ሪፖርትና ምክረ ሀሳብ ለሴቶች፣ ወጣቶችና ማኅበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በተባባሪነት ለሕግ፣ ፍትህና ዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ለዝርዝር እይታ መመራቱ አይዘነጋም።
ምርጫው እንዲካሄድና ዝግጅት እንዲጀመር ምክር ቤቱ ከመወሰኑ ውጪ መቼ እንደሚካሄድ ግን የተሰጠ መረጃ የለም።

LEAVE A REPLY