በሆስፒታል የሚገኘው ድምጻዊ አሊ ቢራ በመልካም ጤንነት ላይ እገኛለሁ አለ

በሆስፒታል የሚገኘው ድምጻዊ አሊ ቢራ በመልካም ጤንነት ላይ እገኛለሁ አለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና|| ህመም አጋጥሞት በሕክምና ላይ የሚገኘው ተወዳጁ የኦሮሚኛ ሙዚቃ ተጫዋቹ ድምጻዊ አሊ ቢራ አሁን በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ተናገረ።

የ73 ዓመቱ አርቲስት አሊ ቢራ ላለፉት ሁለት ሳምንታት በአዲስ አበባ እና አዳማ ከተሞች በሚገኙ ሆስፒታሎች የሕክምና ክትትል ሲያደርግ መቆየቱን አስታውሶ፤ “በፊት ላይ በጣም አሞኝ ነበር። አሁን ተሽሎኛል። አሁን ያለሁበት ሆስፒታል ጥሩ ክትትል እያደረጉልኝ ስለሆነ ፈጣሪ ይመስገን እየተሻለኝ ነው” ሲል ያለበትን የጤንነት ደረጃ ለቢቢሲ ገልጿል።
አንጋፋው ድምጻዊ በአሁኑ ወቅት የውስጥ ደዌ ሕክምና እየተደረገለት ሲሆን ከዚህ ቀደምም የልብ እና የስኳር በሽታዎች ታማሚ መሆኑን ጠቁሟል።
አንዳንድ ሰዎች በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ ስለ እኔ ሐሰተኛ ወሬ በማሰራጨት ሰዎችን እያስደነገጡ መሆኑን ሰምቻለሁ ያለው አሊ ቢራ፤ ሰዎች የመረጃዎችን እውነትነት ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል ሲልም ምክር ለግሷል።
 ሰዎች በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ ያሰራጩት ሐሰተኛ ወሬ እጅጉን እንዳበሳጫት የተናገረችው ባለቤቱ ሊሊ፤ ከእውነት የራቀ መረጃ በመንዛት የተጠመዱ ሰዎች ከዚህ መሰል ተግባራቸው እንዲቆጠቡም ጥሪ አቅርባለች።
የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ሞት ስሜቱን እጅጉን የጎዳው አሊ ቢራ፤ “የዛ ልጅ ሞት እጅግ በጣም ጎድቶኛል . . . ” በማለት ንግግሩን ሳይጨርስ ፊቱ በእንባ መታጠቡን በሆስፒታሉ የተገኘው የቢቢሲ ዘጋቢ አስታውቋል።
የአዳማ አጠቃላይ ሆስፒታል የጤና ኮሌጅ የጤና ባለሙያዎች ጥሩ እንክብካቤ እና የሕክምና ድጋፍ እያደረጉለት እንደሆነ የገለጸው ድምጻዊ አሊ ቢራ፤
ከ 50 ዓመታት በላይ በዘለቀው የሙዚቃ ሕይወቱ፤ በኦሮሞ የሙዚቃ ሥራዎች ውስጥ የራሱን ትልቅ አሻራ ማኖር የቻለ የሙዚቃ ባለሙያ ነው።

LEAVE A REPLY