አዲሱን የብር ኖት 65 በመቶ ለማሰራጨት መቻሉን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገለጸ

አዲሱን የብር ኖት 65 በመቶ ለማሰራጨት መቻሉን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገለጸ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና|| አዲሱን የብር ኖት 65 በመቶ በአገሪቱ ዙሪያ ላሉ የባንክ ቅርንጫፎች ለማሰራጨት መቻሉን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ዶክተር ይናገር ደሴ ተናገሩ።

እስካሁን ባለው ሂደት አዲሱን የብር ኖት ከ3 ሺኅ 960 ቅርንጫፎች በላይ ለማድረስ መቻሉንም ገዢው አስታውቀዋል።
በስርጭት ላይ የሚገኘው አዲሱ የብር ኖት የታተመው በብሔራዊ ባንኩፈክ በመሆኑ ህብረተሰቡ በገንዘቡ ትክክለኛነት ላይ ምንም አይነት ጥርጥር ሊገባው እንደማይገባ ተነግሯል።
የብር ኖት ቅያሬውን በእቅድ ከተያዘው 3 ወራት በፊት ለማጠናቀቅ እየተሠራ መሆኑን ፣ ለአርሶ እና አርብቶ አደር አካባቢዎች ተደራሽ ለማድረግም እየተሠራ እንደሚገኝ ከድክተር ይናገር ደሴ ገለጻ መረዳት ተችሏል።

LEAVE A REPLY