ኢትዮጵያ ነገ ዜና|| የኮቪድ 19 ወረርሽ ከተከሰተ በኋላ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሕዝብ ማመላሻነት ወደ ዕቃ ጫኝነት ከተቀየሩት 25 አውሮፕላኖች መካከል 14ቱ ዳግም ለመንገደኞች ዝግጁ ሆኑ።
በወቅቱ የተከሰተውን የበረራ መቀነስ ተከትሎ አየር መንገዱ ከኪሳራ ለመውጣትና ተወዳዳሪ ሆኖ ለመዝለቅ የዕቃ ጭነት አገልግሎትን ለመስጠት መገደዱ ይታወሳል።
ባለፉት ስድስትና ሠባት ወራት አብዛኞቹ የዓለማችን ሃገራት የአየር ክልላቸውን በመዝጋታቸው ፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድም የሕዝብ ማመላሻ የነበሩትን አውሮፕላኖች ወደ ካርጎ አገልግሎት አውሎ በከፍተኛ ደረጃ ለመንቀሳሰስ ችሏል።
አሁን ላይ ሃገራቱ የአየር ክልላቸውን በመክፈታቸው አውሮፕላቹን ከካርጎ ዳግም ወደ ሕዝብ ማመላሻነት እየተቀየሩ መሆናቸውን ኢትዮጵያ አየር መንገድ የኮርፖሬት ኮሙዩኒኬሽን አስታውቋል።