ኢትዮጵያ ነገ ዜና|| መቐለ 70 እንደርታ እና ፋሲል ከነማ ስፖርት ክለቦች ኢትዮጵያን በአፍሪካ መድረክ ውድድሮች እንዲወክሉ መወሰኑ ተሰማ።
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሼር ካምፓኒ ከትላንት ጀምሮ ጠቅላላ ጉባዔውን እያካሄደ መሆኑን ተከትሎ ዛሬ የተለያዩ ውሳኔዎችን ያሳለፈ ሲሆን፤ ከእነዚህ መካከልም ኢትዮጵያን በአህጉራዊ መድረክ ወክለው የሚሳተፉ ክለቦችም ተለይተዋል፡፡
በውሳኔው መሠረት በ2011 ዓ.ም መቐለ 70 እንደርታ የፕሪምየር ሊግ ሻምፒዮን በመሆኑ በካፍ ሻምፒዮንስ ሊግ እንዲሳተፍ ሲወስን፣ የጥሎ ማለፍ ዋንጫ ሻምፒዮኑ ፋሲል ከነማ በኮንፌዴሬሽን ዋንጫ እንዲሳተፍ መወሰኑን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በማህበራዊ ትስስር ገጹ ይፋ አድርጓል።