በአዲስ አበባና ኦሮሚያ ልዮ ዞን ትምህርት ጥቅምት 30 እንዲጀመር ተወሰነ

በአዲስ አበባና ኦሮሚያ ልዮ ዞን ትምህርት ጥቅምት 30 እንዲጀመር ተወሰነ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በኢትዮጵያ የሚገኙ ትምህርት ቤቶች በሦስት ዙር ትምህርት እንዲጀምሩ ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁን ሚኒስቴር ዛሬ ይፋ አደረገ።

በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ተቋርጦ የነበረውን ትምህርት ቤቶችን ዳግም መክፈት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ በጠቅላይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት እየተደረገ ባለው ውይይት ላይም ይህ እቅድ መቅረቡ ታውቋል።
በውይይቱ ላይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀን ጨምሮ፣ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች የክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎችና ሌሎች ሚኒስትሮችም የተገኙ ሲሆን፤ የትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁንም በሦስት ዙር የሚከናወነውን ትምህርት የማስጀመር ሂደትን በተመለከተ ምክረ  ሀሳባቸውን በዝርዝር አቅርበዋል።
ይህን ተከትሎ በገጠር ወረዳና ቀበሌ ከተሞች የሚገኙ ትምህርት ቤቶች መጀመሪያ በተባለው ዙር ጥቅምት 9/2013 ዓ.ም፣ በሁሉም ዞንና የክልል ከተሞች የሚገኙ ትምህርት ቤቶች በ2ኛው ዙር ጥቅምት 16/2013 ዓ.ም ትምህርት እንዲጀምሩ ሀሳብ ቀርቧል።
በአዲስ አበባና በኦሮሚያ ክልል ልዩ ዞን የሚገኙት ትምህርት ቤቶች ፤ ትምህርት ሚኒስቴር ሦስተኛ ዙር ብሎ ባስቀመጠው ጥቅምት 30/2013 ዓ.ም ይጀምሩ የሚል ምክረ ሀሳብ በውይይቱ ላይ ቀርቧል።
የብሔራዊ ፈተና የሚወስዱ የ8ኛና የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ሁሉም ለፈተና እንዲቀመጡ፣ የ8ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናም ህዳር 22 እና 23/2013 ዓ.ም እንዲወስዱ እቅድ የተያዘ ሲሆን፤ ፈተና ላይ መቀመጥ የሚችሉት ተማሪዎች የ7ኛ ክፍልን ተምረው ያጠናቀቁና የ8ኛ ክፍል አንደኛ መንፈቀ ዓመት ትምህርትንም የተከታተሉ ሊሆኑ እንደሚገባም ሚኒስቴሩ መ/ቤቱ አስታውቋል።
ለ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና መቀመጥ የሚችሉት የ11ኛ ክፍልን አጠናቀው ያለፉና የ12ኛ ክፍል የመጀመሪያ መንፈቀ ዓመት ትምህርት የተከታተሉ ሊሆኑ እንደሚገባም እና
 መልቀቂያ ፈተናው  ከህዳር 28 አስከ ታህሳስ 1/2013 ዓ.ም እንደሚሆን ከቀረበው ምክረ ሀሳብ መረዳት ተችሏል።

LEAVE A REPLY